አዲስ አበባ፤ የካቲት 13/2017(ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ልህቀት አካዳሚ ከሸገር ከተማ አስተዳደር፣ ከኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት እና ከፓን አፍሪካ ወጣቶች ህብረት ጋር በትብብር መስራት የሚያስችለውን የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ።
ስምምነቱን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት ዛዲግ አብርሃ፣ የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተሾመ አዱኛ(ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ፉአድ ገና እንዲሁም የፓን አፍሪካ ወጣቶች ህብረት ዋና ፀሐፊ ዊዚቾንግ ቤኒንግ አህመድ ፈርመዋል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ አካዳሚው በዛሬው እለት ከሶስት ተቋማት ጋር በትብብር መስራት የሚያስችሉትን ስምምነቶች መፈራረሙን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ የእድገት ግስጋሴ እውን እንዲሆን የዘመኑ ከተሞችን መገንባትና ማልማት እንዲሁም ከተሞችን የሚመሩ አመራሮችን አቅም ማሳደግ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
ለዚህም አካዳሚው የሸገር ከተማ አስተዳደር አመራሮችን አቅም ለማጎልበት እና ሌሎች ተያያዥ ተግባራትን ለማከናወን እንደሚሰራም ጠቁመዋል።
በተመሳሳይ ወጣቶችን በአመራርነት ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ማሳደግ የሚያስችል አቅም ለመፍጠር ከኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት እና ከፓን አፍሪካ ወጣቶች ህብረት ጋር በትብብር ይሰራል ብለዋል።
የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተሾመ አዱኛ(ዶ/ር) የከተማዋን እድገት በማፋጠን ተወዳዳሪ ብሎም ለማህበረሰቡ ቀልጣፋ እና የዘመነ አገልግሎትን መስጠት የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።
ነገር ግን ከተማዋን ለማዘመን በተወሰነ አካል ብቻ በሚሰራ ስራ የሚፈለገውን ውጤት ማምጣት አዳጋች መሆኑን ገልጸው ከተለያዩ ተቋማት ጋር በትብብር መስራት ይጠይቃል ብለዋል።
በተለይም አንድን ከተማ እውቀትን በአግባቡ በመጠቀም ማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራትን ማከናወን የሚጠይቅ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለዚህም በጥናትና ምርምር እንዲሁም በስልጠና ላይ ከሚሰሩ ተቋማት ጋር በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ይህን መነሻ በማድረግ የከተማ አስተዳደሩ የአቅም ግንባታና ሌሎች ለከተማው የሚጠቅሙ ስራዎችን ከአካዳሚው ጋር ለመስራት ስምምነቱ መፈረሙን ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ፉአድ ገና እና የፓን አፍሪካ ወጣቶች ህብረት ዋና ፀሐፊ ዊዚቾንግ ቤኒንግ አህመድ በበኩላቸው የወጣቶችን የአመራርነት አቅም ለመገንባትና ሌሎች ከወጣቶች ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ስምምነቱ ትልቅ ጠቀሜታ እንደሚያበረክት ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025