የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

<p>በለውጡ ዓመታት በጎንደር የተከናወኑት የልማት ተግባራት የከተማውን ገጽታ በተጨባጭ የቀየሩ ናቸው</p>

Feb 24, 2025

IDOPRESS

ጎንደር፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በለውጡ ዓመታት ጎንደርን የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ብልጽግና ፓርቲ ያከናወናቸው የልማት ተግባራት የከተማውን ገጽታ በተጨባጭ የቀየሩ መሆናቸውን የሕዝባዊ ኮንፍረንስ ተሳታፊዎች ተናገሩ፡፡

"ከቃል እስከ ባህል" በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀ ሕዝባዊ ኮንፈረንስ ዛሬ ተካሄደዋል።

ከኮንፍረንሱ ተሳታፊዎች መካከል አቶ እሸቱ በላይ በሰጡት አስተያየት፤ ፓርቲው በለውጡ ዓመታት ያስመዘገባቸው ውጤቶች ሀገርን በማሻገር ሩቅ ማድረስ እንደሚቻል አመላካች መሆናቸውን ተናግረዋል።


ባለፉት ስርዓቶች ጎንደር በታሪኳና በእድሜዋ ልክ የልማት ተቋዳሽ መሆን የሚያስችላት እድል አላገኘችም ሲሉ አውስተዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ለከተሞች የተመጣጠነ እድገትና ልማት በሰጠው ልዩ ትኩረት ከተማዋ በአሁኑ ወቅት የኮሪደር ልማትን ጨምሮ ታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶች ተጠቃሚ ለመሆን በቅታለች ብለዋል፡፡

ለፓርቲው ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ተፈጻሚነት የድርሻቸውን እንደሚወጡም ገልጸዋል።

ሌላው ተሳታፊ አቶ ጓዴ ደመቀ፤ በከተማው እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች በሀዝቡ ዘንድ ትልቅ መነሳሳትንና ቁጭትን የፈጠሩ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከተማዋ ያገኘችው የልማት እድል ተጠናክሮ እንዲቀጥል መንግስት ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ እያደረገ ያለውን ጥረት በመደገፍ የድርሻዬን ለመወጣት ዝግጁ ነኝ ብለዋል፡፡

በለውጡ ዓመታት የብልጽግና ፓርቲ ያከናወናቸው ዘርፈ ብዙ የልማት ተግባራት የህዝቡን ተስፋና ምኞት ያለመለሙ ናቸው ያሉት ደግሞ ወይዘሮ ካሳነሽ አዲሱ ናቸው፡፡

በከተማው አሁን ላይ በሰፈነው ሰላም የልማት ተቋዳሽ መሆን ጀምረናል፣ ልጆቻችንም የስራ እድል የሚያገኙበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል ያሉት ወይዘሮ ካሳነሽ፤ የልማቱ መሰረት የሆነውን ሰላም ለማጽናት አበክረው እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡


በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጂጌ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በጎንደር ከተማ የሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ የተጀመረው ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

አመራሩ ለፓርቲው ውሳኔዎች ተግባራዊነት በላቀ ቁርጠኝነት ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ጠቁመው፣ ህዝቡ ልማት እንዲፋጠን እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠንክሮ እንዲቀጥልም መልዕክት አስተላልፈዋል።


ብልጽግና ፓርቲ በለውጡ ዓመታት ለህዝቡ የገባውን ቃል በተግባር ያረጋግጣል ያሉት ደግሞ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ(ዶ/ር) ናቸው።

የፓርቲው ጉባኤ ውሳኔዎች የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ሀገር የማሻገር ተልዕኮ ያነገቡ መሆናቸውን ጠቁመው፤ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ ህዝቡ በጋራ መቆምና መሳተፍ እንዳለበት አመልክተዋል

የጎንደር ህዝብ ሰላም፣ ልማት ወዳድና እንግዳ አክባሪ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ የተጀመሩ የልማት ስራዎች በላቀ ጥራትና ፍጥነት ተጠናቀው ለህዝብ አገልግሎት እንዲውሉ የፌዴራል መንግስት ይደግፋል ብለዋል፡፡

በኮንፍረንሱ ከከተማው የተለያዩ ቀበሌዎች የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ምሁራን፣ ሴቶችና ወጣቶች ተሳትፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.