ደብረብርሀን፤ የካቲት 15ቀን 2017(ኢዜአ) አገራዊ ለውጡን ተከትሎ በደብረብርሀን ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የኢንቨስትመንት ተግባራት የአገራችን የኢኮኖሚ እድገት መገለጫ ናቸው ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚና በፓርቲው የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ ገለጹ።
የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በደብረ ብርሀን ከተማ የሚገኙ ዋን ወይ የጨርቃጨርቅና አልባሳት ፋብሪካንና ጅንሹ ኢትዮጵያ የቴክስታይል ቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪዎችን ዛሬ ጎብኝተዋል።
አቶ አብርሃም ማርሻሎ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ በደብረ ብርሀን ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ስራዎች የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ያደረጉ ናቸው።
በተለይም በከተማዋ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ የአካባቢውን የቱሪዝም ልማት ለማሳደግና ለስራ እድል ፈጠራ መልካም አጋጣሚን የሚፈጥር ነው ብለዋል።
የደብረ ብርሀን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት በበኩላቸው፥ በከተማዋ ሰላምን ከማጽናት ጎን ለጎን የንግድና የኢንቨስትመንት ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ባለፉት ሰባት ወራት 17 ኢንዱስትሪዎች ወደ ማምረት መሸጋገራቸውን ጠቁመው፥ የተካሄደው ጉብኝትም ከከፍተኛ አመራሮች በሚገኝ ግብዓት በቀጣይ የላቀ ልማት ለማከናወን ያግዘናል ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025