ሮቤ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፦ የሲኮ መንዶ የአርሶ አደሮች ህብረት ሥራ ዩኒየን ለ2017/18 የበልግ ወቅት የሚውል 540 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ እያቀረበ መሆኑን ገለጸ።
የዩኒየኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ታዬ እንደገለጹት፥ ዩኒየኑ ለዘንድሮው የበልግ ወቅት የሚውል 540 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ እያቀረበ ነው።
ዩኒየኑ በእስካሁኑ ሂደት ካቀረበው ከ100 ሺህ በላይ የአፈር ማዳበሪያ 50 በመቶ የሚሆነው ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱን አመልክቷል።
በተለይም ዩኒየኑ ቀደም ሲል ይስተዋል የነበረውን የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ችግር በመቅረፍ በተከናወኑ የማሻሻያ ስራዎች የተሻለ የሥርጭት ሂደት መመዝገቡን ተናግረዋል።
የአፈር ማዳበሪያውን ወደ ዞኑ የማጓጓዝ ስራው በተጠናከረ መልኩ እየተከናወነ ሲሆን በየቀኑ 25 መኪና የአፈር ማዳበሪያ ወደ ዩኒየኑ መጋዘን እንደሚገባም አረጋግጠዋል።
ዩኒየኑ የአርሶ አደሩን የማምረት አቅም የሚጨምሩ ከ100 ሺህ ሊትር የሚበልጡ የተለያዩ አይነት ኬሚካሎችን ለማቅረብ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
የዞኑ የህብረት ሥራ ማህበራት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ምክትል ኃላፊ አቶ ደበሌ ሀቤቤ በበኩላቸው፥ በዞኑ የአርሶ አደሩን የማምረት አቅም የሚጨምሩ ግብዓቶችን በወቅቱ ለማቅረብ ትኩረት መሰጠቱን ገልፀዋል።
በዞኑ ምርትና ምርታማነትን በመጨመር በምግብ ራስን ለመቻል የሚከናወኑ ተግባራትን ከዳር ለማድረስ 3 ዩኒየኖችና 34 የህብረት ሥራ ማህበራት በማዳበሪያና ሌሎች የግብርና ግብዓቶች ስርጭት ላይ እየሰሩ መሆኑንም አክለዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025