ባህርዳር፤ የካቲት 18/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል የሚሰበሰበውን ገቢ በአግባቡ በማስተዳደር ለልማት ስራዎች ማዋል እንደሚገባ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ አስገነዘቡ።
"ግብር፣ ለሀገር ክብር" በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀ የዕውቅናና የታክስ ንቅናቄ መድረክ በባህር ዳር ከተማ ተካሂዷል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በመድረኩ ላይ እንዳሉት፤ ክልሉ ካለበት ነባራዊ ሁኔታ አኳያ ገቢ የመሰብሰብ አቅምን በማሳደግ ሀብት መፍጠር ያስፈልጋል።
ለዚህም የገቢ አማራጮችን ለማስፋት ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ሲሆን የሚሰበሰበውን ገቢም በአግባቡ ማስተዳደርና ለልማት ስራዎች ማዋል እንደሚገባ ገልፀዋል።
ገቢን በትልቁ መሰብሰብ ልማቱን ከማፋጠን በተጨማሪ የተረጋጋ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታ እንዲፈጠር አስቻይ መሳሪያ በመሆኑ ሁሉም አካል ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
ባለፈው ዓመት ክልሉ በአስቸጋሪ የጸጥታ ችግር ውስጥ ሆኖም ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡና ለዕውቅና ሽልማቱ ለበቁ የክልሉ ግብር ከፋዮች ምስጋና አቅርበዋል።
የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ክብረት ሙሀመድ በበኩላቸው፤ ሀገራዊ የገቢ ሪፎርም የክልሉን ገቢ የመሰብሰብ አቅም በአራት እጥፍ ማሳደግ አስችሏል ብለዋል።
የክልሉን የጸጥታ ችግር እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ህገወጥ አሰራርን የተከተሉ ግለሰቦች መኖራቸውን ጠቅሰው በርካታ የክልሉ ግብር ከፋዮች ግን ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በመወጣታቸው የተሻለ ገቢ እንዲሰበሰብ ማስቻሉን ገልፀዋል።
በክልሉ ባለፉት ሰባት ወራትም ከ31 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ እንደተቻለ ገልፀው፤ ይህን የተሻለ አሰራር በማጎልበት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
የዚህ መድረክ ዓላማም የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ የተወጡትን ለማበረታታትና ዕውቅና ለመስጠት መሆኑንም አክለዋል።
በመድረኩ የክልሉና የፌዴራል አመራሮች እንዲሁም ምስጉን ግብር ከፋዮች ተሳትፈዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025