ባህር ዳር፤ የካቲት 18/2017(ኢዜአ)፡-የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የአማራ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በባህርዳር ከተማ እየተከናወነ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ጎበኙ።
ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎቹ የጎበኙት በከተማው ከድሮው ጊዮን ሆቴል እስከ አጅፕ በመጀመሪያ ምዕራፍ የተገነባውን የኮሪደር ልማት ነው።
የባህርዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው፤ በከተማው 22 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ለመስራት ታቅዶ የመጀመሪያው ምዕራፍ 3 ኪሎ ሜትር እየተጠናቀቀ መሆኑ ተናግረዋል።
የስራ ኃላፊዎቹ ከኮሪደር ልማት ስራው በተጨማሪም በከተማዋ እየተገነቡ የሚገኙ ሌሎች የልማት ስራዎችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በጉብኝቱ ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አስተባባሪና የአማራ ክልል ከተሞችና መሰሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አህመዲን መሀመድ (ዶ/ር)፤ የጉሙሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025