የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

<p>ኢትዮጵያ ለስምምነቱ ተግባራዊነት በቁርጠኝነት ትሰራለች - ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)</p>

Feb 28, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለኮሪደር ባለስልጣን መመስረቻ ስምምነቱ ገቢራዊነት በቁርጠኝነት እንደምትሰራ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገለጹ።

ለሁለት ቀናት በጅቡቲ የተካሄደው የኮሪደር አስተዳደር ባለስልጣን ምስረታ የሚኒስትሮች መድረክ የጅቡቲ-ኢትዮጵያ-ደቡብ ሱዳን-ዩጋንዳ (DESSU) ኮሪደር ባለስልጣን መመስረቻ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትናንት ማምሻውን ተጠናቋል።


የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ታሪካዊው ስምምነት በአፍሪካ ቀንድ እና ምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ንግድ፣ ትስስር እና ኢኮኖሚያዊ ትብብርን እንደሚያጠናክር በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ለስምምነቱ ትግበራ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ እና በኮሪደሩ አማካኝነት የጋራ ብልጽግናን እውን እንዲሆን የበኩሏን ድርሻ እንደምትወጣም አረጋግጠዋል።

በስምምነቱ አማካኝነት ቀልጣፋ የሎጂስቲክስ አገልግሎት፣ ትብብሩ እንዲጠናከር እና ለሀገራቱ መጻዒ ጊዜው ብሩህ እንዲሆን የሚያስችል መንገድ ከፍተናል ብለዋል ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.