አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት እና አድዋ የአዲሱ ትውልድ የአንድነት መገለጫና የኩራት ምንጮች መሆናቸውን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ገለጸ።
የህዳሴ ግድብ በድህነት ላይ የተጎናጸፍነው ዳግም የዓድዋ ድል ነው ሲልም ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ለ129ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአድዋ ድል በዓል አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
በመልዕክቱም ሁለተኛው የዘመናችን አድዋ የሆነው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት እና አድዋ የአዲሱ ትውልድ የአንድነት መገለጫና የኩራት ምንጮች ናቸው ብሏል።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት እና አድዋ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን በአንድነት ለልማት ያስነሱ አርማዎች መሆናቸውንም አመልክቷል።
አባቶቻችን ሀገርን ለወራሪ ላለማስደፈር በዱርና በገደል በአርበኝነት ተፋልመው ሀገርን እንዳስከበሩ ሁሉ የአሁን ትውልድም አይደፈርም ብሏል።
በብድርና እርዳታ አይሰራም ተብሎ የሚታሰበውን አባይን ለማልማት በህብረት ተረባርቦ በማስጀመር፣ በመምራትና አሁን ለሚገኝበት ደረጃ ማድረስ የህዝቡ ትልቅ ድል መሆኑን ነው የገለጸው።
ከመላው ህዝብ እስከ እሁን ለህዳሴ ግድብ ከ21 ቢሊየን ብር በላይ የፋይናንስ ድጋፍ መሰብሰቡንና የግድቡ አጠቃላይ አፈጻጸም በአሁኑ ወቅት ከ98 በመቶ በላይ መድረሱን ጠቁሟል።
ፕሮጀክቱ ትውልዱ በቅብብሎሽ ሲዘክረው የሚኖር በድህነት ላይ የተከፈተ 2ኛው የአድዋ ድል ገጽ ያለው ዘመቻ ነውም ብሏል በመልዕክቱ።
ያላሰለሰ የኢትዮጵያውያን፣ ትውልድ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሁለንተናዊ ተሳትፎ መስዋ”ትነት የተከፈለበት እንደሆነም ተመላክቷል።
ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብቷ እንዳትለማ የቅርብ እና ሩቅ ጠላቶች ለዘመናት ጥረት ቢያደርጉም በኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ የጋራ ርብርብ የተፋሰስ ሀገራቱን የስምምነት ማዕቀፍ በማጽደቅ በቀጣናው የክፍለ ዘመኑን ከፍተኛ ድል ተመዝግቧል ነው ያለው ጽህፈት ቤቱ።
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት መላው ኢትዮጵያ ህዝብን ብሎም የተፋሰሱ ሀገራትን ህዝቦች በጋራ የማደግ ፍላጎት ጥላ ስር ያሰባሰበ፣ በቀጣናው የይቻላልን መንፈስ በተግባር ያረጋገጠ በድህነት ላይ የተጎናጸፍነው ዳግም ዓድዋ ድል እንደሚያደርገው አመልክቷል።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ፕሮጀክቱ በዜጎች እና መንግስት የነቃ ተሳትፎ ቅብብሎሽ የማጠቃለያ ምዕራፍ ላይ በመድረሱ የሚያኮራ መሆኑንም ነው የገለጸው።
ጽህፈት ቤቱ ህዝቡ ግድቡ እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርቧል።
በህዝባዊ ተሳትፎና በጀግንነት የጀመርነውን ግድብ በአርበኝነት እናጠናቅቀዋለን ነው ያለው በመልዕክቱ።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025