አዲስ አበባ፤ የካቲት 24/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ሀገራዊ ዕቅዶችና አቅጣጫዎች በውጤታማነት እንዲፈጸሙ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለፀ፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ሠራተኞች በቀጣይ ሶስት ዓመታት ተግባራዊ በሚደረጉ የመንግስት አቅጣጫዎች እና ውሳኔዎች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሂደዋል፡፡
በውይይቱም ባለፉት ዓመታት የሕዝቦችን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ፣ የሀገርን የዕድገት አቅጣጫ ያመላከቱ እንዲሁም የብሔራዊነት ገዥ ትርክትን ማስረጽ የሚያስችሉ ታላላቅ ተግባራት መከናወናቸው ተገልጿል፡፡
የመንግስት ውሳኔዎችንና አቅጣጫዎችን በተመለከተ ገለጻውን ያቀረቡት የኢዜአ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ነጋሲ አምባዬ፤ በሀገር ደረጃ ባለፉት ዓመታት የሕዝቦችን አንድነት ለማጠናከር፣ የፖለቲካ ምህዳርን ለማስፋት፣ ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት እንዲሁም የኢኮኖሚ ዕድገትን ከማፋጠን አንጻር አመርቂ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡
በመጪዎቹ ሶስት አመታትም የብሔራዊ ገዥ ትርክት እና የሰላም ግንባታን ውጤታማ የማድረግ ስራዎች ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ጠቅሰው፤ የፍትህ ዘርፉን ከማሳደግ አንጻርም በቴክኖሎጂ የተደገፉ ስራዎች እንደሚሰሩ አብራርተዋል።
የኢኮኖሚ ልማትን ከማፋጠን አኳያም ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግና የወጪ ንግድን በማስፋት በኩል ትኩረት መሰጠቱን አንስተዋል።
ማህበራዊ ብልጽግናን የሚያረጋግጡ የጤና፣ ትምህርት እና ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮችን ውጤታማ የሚያደርጉ ስራዎች እንደሚሰሩም አብራርተዋል፡፡
ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸው፤መርኸን እና እውነትን መሠረት ያደረጉ ስራዎች እንደሚጠናከሩም አንስተዋል፡፡
አስተያየታቸውን የሰጡ የተቋሙ ሰራተኞች ኢዜአ መንግስት በአቅጣጫና ውሳኔ ያሳለፋቸው ነጥቦች ተገንዝቦ በመስራት ለስኬታማነታቸው የበለጠ ጠንክረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሰይፈ ደርቤ በሰጡት ማጠቃለያ ሃሳብ የተቋሙ ሰራተኞች የመንግስትን አቅጣጫዎችን ተገንዝቦ በመስራት ሀገራዊ ሃላፊነትን በብቃት መፈጸም ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
መንግስት የሀገርን ብልፅግና ለማረጋገጥ እያከናወናቸው የሚገኙ ሁሉን አቀፍ አቅጣጫዎችን በማሳካት በኩል የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ እንዲሁ።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025