አዲስ አበባ፤ የካቲት 25/2017(ኢዜአ)፦ በሸገር ከተማ አስተዳደር በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያ ዙር 502 ሞደል አርሶ አደሮች ወደ ኢንቨስትመንት መሸጋገራቸውን የአስተዳደሩ የኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ሃላፊ ሀይለሚካኤል አለሙ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት የከተማ አስተዳደሩ አሰራሮችን ምቹ በማድረግ ባለሀብቶች በማኑፋክቸሪንግ፤ በአገልግሎት አሰጣጥና በግብርና ዘርፎች ተሰማርተው እንዲያለሙ የኢንቨስትመንት ቅበላ እያደረገ ይገኛል።
በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያ ዙር 502 ሞዴል አርሶ አደሮችን ወደ ኢንቨስትመንት ማሸጋገሩን ገልጸው፤ ይህም አርሶ አደሮቹ በኢኮኖሚው እንቅስቃሴ ውስጥ የድርሻቸውን እንዲያበረክቱ ያስችላል ብለዋል።
በዚህም በኢንቨስትመንት እንቅስቃሴው ከ25 ሺህ በላይ ዜጎች የስራ እድል የሚፈጠርላቸው መሆኑንም ተናግረዋል።
የከተማ አስተዳደሩ በግብርናው ዘርፍ ለአከባቢው አርሶ አደሮች ተጠቃሚነት ቅድሚያ በመስጠት ባላቸው እውቀትና ልምድ በዘርፉ እንዲያለሙ ማድረጉንም አስታውቀዋል።
በዚህም በኢንቨስትመንቱ ህብረተሰቡን የስራ እድል ተጠቃሚ በማድረግ በኢኮኖሚው እንቅስቃሴ ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል።
በከተማው ባለፉት ሁለት ዓመታት የኢንቨስትመንት ቅበላው በተለያዩ ምክንያቶች የቆመ ቢሆንም የአካባቢውን ሞዴል አርሶ አደሮችን በልዩ ሁኔታ እየተቀበለ መቆየቱን ተናግረዋል።
በዚህም 273 ሞዴል አርሶ አደሮቹን ወደ ኢንቨስትመንት እንዲሸጋገሩ ማድረጉን አስታውቀዋል።
ሸገር ከተማ እንደ አዲስ ከመመስረቱ በፊት በኢንቨስትመንት ውጤታማነት ምጣኔ 44 በመቶ ሲሆን ባለፉት ሁለት ዓመታት በተከናወኑ ተግባራት ወደ 54 በመቶ ማደግ መቻሉን አክለዋል ሀላፊው።
በከተማው ወደ ኢንቨስትመንት እየተሸጋገሩ ያሉ ባለሀብቶች በውጤታማነት ላይ ትኩረት በማድረግ መስራት እንዳለባቸው አሳስበው የወሰዱትን መሬት በተሰጣቸው ጊዜ ውስጥ አልምተው የስራ እድል በመፍጠር በኢኮኖሚው ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ አስገንዝበዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025