አዲስ አበባ፤የካቲት 25/2017(ኢዜአ)፦በቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት የበልግ አብቃይ አካባቢዎች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ ይጠበቃል ሲል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
ኢንስቲትዩቱ በኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፥በቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት ለዝናብ መፈጠር አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች እንደሚጠናከሩ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ከዚህ ጋር ተያይዞ በደቡብ፤ በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ ምዕራብ እንዲሁም በስምጥ ሸለቆና አጎራባች አካባቢዎች የተሻለ ጥንካሬ ይኖራቸዋል ብሏል።
በዚህም የበልግ አብቃይ አካባቢ በሆኑት የመካከለኛው፣የሰሜን ምስራቅ፣ የደቡብ ምዕራብ እና የደቡብ የሀገሪቱ አካባቢ ያሉ በርካታ ቦታዎችን ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙም ተጠቁሟል።
አልፎ አልፎ በሚጠናከሩ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በደቡብ፤ በመካከለኛው፣በሰሜን ምስራቅ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙም ትንበያው አመላክቷል።
በጋምቤላ፣ በአፋር፣ በሶማሌ፣ በቤንሻንጉል-ጉሙዝና በምዕራብ አማራ አካባቢዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት ከ35 እንዲሁም በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ከ40 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች እንደሚያሳዩ ተገልጿል።
በቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ እና በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የሚጠበቀው እስከ መካከለኛ መጠን ያለው እርጥበት ለበልግ የእርሻ ስራ እንቅስቃሴ አዎንታዊ ጠቀሜታ እንዳለው ተጠቁሟል።
በልግ ተለዋዋጭ ባህሪ ጋር ተያይዞ የሚኖሩት ደረቅ ሰሞናት እና ከፍተኛ የትነት መጠን የአፈር ውስጥ እርጥበት እጥረት እንዲኖር እንደሚያደርግ ተገልጿል።
አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች እና የሚመለከታቸው አካላት በሚሰጡ የግብርና ምክረ ሃሳብ መሰረት የቅድመ ጥንቃቄ ተግባራትን ማከናወን እንዳለባቸውም ተጠቁሟል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025