አዲስ አበባ፤ የካቲት 26/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት በኢነርጂ ዘርፍ የሕዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጅነር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ከለውጡ ወዲህ በኢነርጂው ዘርፍ በኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት ብሎም የጸሐይ ኃይል ማመንጫዎችን ከማስፋፋት አኳያ እና በሌሎችም አመርቂ ስራዎች መከናወናቸውን አክለዋል፡፡
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጅነር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ከለውጡ ወዲህ የኃይል ማመንጨት አቅምን ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሂደት በለውጡ መንግስት ልዩ ክትትል አሁን ያለበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ በልዩ ጥበብና ብልኃት መመራቱን ጠቁመዋል፡፡
በኢትዮጵያ በኢነርጂው ዘርፍ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ያነሱት ሚኒስትሩ፤ ከጠቅላላ የህዝብ ብዛት 54 በመቶ የሚሆኑት የኃይል ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ይህም ከለውጡ ወዲህ ከ6 በመቶ በላይ ዕድገት ማሳየቱንም ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በውሃና ኢነርጂ ዘርፎች የሚያደርጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው በዚህም ዘርፉ በአመርቂ የዕድገት ደረጃ ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በኢነርጂው ዘርፍ ከ5 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ቆጣሪ ያላቸውን ደንበኞች ማፍራት መቻሉን ጠቁመዋል፡፡
እንደ ሀገር ኃይል የማመንጨትና የማቅረብ አቅም እያደገ መምጣቱን አንስተዋል፡፡
በማመንጨት አቅም እንደ ሀገር ታላቅ ስኬቶች መመዝገባቸውንም የገለጹት ሚኒስትሩ ባለፉት ስድስት ወራት ከ320 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞች መገኘታቸው ተናግረዋል፡፡
ከዋናው መስመር የራቁ አካባቢዎችን የኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ በጸሐይ ኃይል መማንጫ ሶላር ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል፡፡
በዚህም በሶማሌ፣ ኦሮሚያ፣ አፋር እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ዳሰነች አካባቢዎችን ከ10 ሺህ በላይ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
የጸሐይ ኃይል ማመንጫዎችን በትምህርት ተቋማትና በሌሎችም የማዳረስ ስራዎች ላይ ትልቅ ውጤት መገኘቱን ጠቁመዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025