
ደሴ፤ መጋቢት 1/2017(ኢዜአ)፡- በደሴ ከተማ አስተዳደር እየተከናወነ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት በጥራትና በፍጥነት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ ገለፁ፡፡
በደሴ ከተማ ከቧንቧ ውሃ-ሮቢት እየተገነባ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የአስፋልት ንጣፍ ሥራ ዛሬ ተጀምሯል፡፡

ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በማስጀመሪያ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት በከተማው እየተገነባ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ለከተማዋ እድገትና ለህዝቡ ተጠቃሚነት አዲስ ምዕራፍን የከፈተ ነው፡፡
የኮሪደር ልማት ግንባታውን በጥራትና በፍጥነት በማጠናቀቅ ለህዝብ ጥቅም ለማዋል ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ለዚህም ከቧንቧ ውሃ-ሮቢት እየተገነባ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የአስፋልት ንጣፍ ሥራ ዛሬ መጀመሩ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
የኮሪደር ልማት የብስክሌትና የእግረኛ መንገድን ጨምሮ ሌሎች መዝናኛ ሥፍራዎችን ያካተተ በመሆኑ ለጎብኚዎችና ለነዋሪዎች መዝናኛነት ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ገልጸዋል፡፡

በኮሪዳር ልማቱ የአካፋይ መንገድ፣ የመብራት ፖል ዝርጋታ፣ የካናል ስራ፣ የውሀ መስመር ዝርጋታና ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
ለልማቱ ህብረተሰቡ ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን ጠቁመው እስካሁን ከ150 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡
በደሴ ከተማ ከቧንቧ ውሃ-ሮቢት-ወሎ ባህል አምባ አንድ 1 አንድ 18 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተመልክቷል፡፡
አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...
Sep 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...
Aug 31, 2026
ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Aug 17, 2026
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...
Jul 27, 2026