የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

ኢትዮጵያ እና ኮሪያ ሪፐብሊክ በትብብር ለመስራት ተስማሙ

Mar 12, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 2/2017 (ኢዜአ):- የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በኢትዮጵያ የኮሪያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ጁንግ ካንግ ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።

ሚኒስትሯ ከአምባሳደር ጁንግ ጋር ኢትዮጵዮጵያ እና ኮሪያ ሪፐብሊክ በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

ኢትዮጵያና ኮሪያ ሪፐብሊክ ዘመናትን የተሻገረ ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት እንደሆኑም አውስተዋል።

በውይይቱ በክህሎት ልማት እንዲሁም የእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራዎች ላይ በትብብር ለመስራት ከመግባባት ላይ መደረሱን አመልክተዋል።

ኮሪያ ሪፐብሊክ በቴክኒክና ሙያ ዘርፉ ለኢትዮጵያ ጠንካራ ድጋፍ ከሚያደርጉ ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗን ገልጸው ይህም ትብብሩን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ እንደሚያደርገው ተናግረዋል።

ሚኒስትሯ ለአምባሳደር ጁንግ የሀገራቱን የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት በማድረግ ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ላሳዩት ቁርጠኝነት ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.