ወልቂጤ፤ መጋቢት 2/2017(ኢዜአ)፦ የጊቤ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክን ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ገለፀ።
የፓርኩን ህልውና ለመታደግ በፓርኩ ወሰን ዙሪያ ከሚገኙ ባለድርሻ አካላትና የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በወልቂጤ ከተማ ምክክር ተካሂዷል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትልና የቱሪዝም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኑሪ ከድር በፓርኩ የሚስተዋሉ ችግሮችን በጥናት ለይቶ በመፍታት ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
በፓርኩ ጽህፈት ቤት የሪፎርም ሥራ ከተከናወነ ወዲህ የሀገር ውስጥ ጎብኚዎችን ቁጥር ማሳደግ መቻሉንም ተናግረዋል።
በፓርኩ ውስጥ በርካታ የቱሪስት መስህቦች ቢገኙም የመሰረተ ልማት አለመስፋፋት ከዘርፉ የሚፈለገው ጥቅም እንዳይገኝ አድርጓል ነው ያሉት።
በመሆኑም የመሰረተ ልማት ችግሩን ለመፍታት ቢሮው ከክልሉ ገጠር መንገድ ጋር የውል ስምምነት በመፈራረም ወደ ተግባር መገባቱን አስታውቀዋል።
ከክልሉ ዲዛይንና ቁጥጥር ባለስልጣን ጋር በመቀናጀት የቱሪስት ማረፊያዎችን ለማስገንባት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
እንደ ኃላፊው ገለፃ የፓርኩን ህልውና እየተፈታተነ ያለውን ህገወጥ ሰፈራ በዘላቂነት ለማስቆምም ከጉራጌ ዞን አስተዳደር እና ከፓርኩ አዋሳኝ ወረዳዎች እንዲሁም ከጸጥታ መዋቅሮች ጋር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ መሰረት አመርጋ በበኩላቸው እንዳሉት በጊቤ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ የተለያዩ የዱር እንስሳት ዝርያዎች፣ ፍል ውሃዎችእና ሌሎች የመስህብ ስፍራዎች ይገኛሉ።
የፓርኩ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ መንግስቱ ሙሉጌታ ፓርኩ የአካባቢውን ስነ ምህዳር ለማስጠበቅ ያለው አበርክቶ ከፍተኛ በመሆኑ ህብረተሰቡን በማሳተፍ ህገወጥ ሰፈራን ለማስቆም ይሰራል ብለዋል።
በጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ የቱሪዝም አገልግሎት እና ግብይት ባለሙያ ወይዘሮ ወይንሸት ሰተቶ በበኩላቸው በፓርኩ መሰረተ ልማት በመሟላትና በማስተዋወቅ ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
የፓርኩን ብዝሃ ህይወት ለመጠበቅ ክትትልና ቁጥጥር ከማድረግ ባለፈ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ እንደሚገባ የገለጹት ደግሞ የፓርኩ ስካውት ጭቅሶ ቱሪ ናቸው።
በምክክር መድረኩ የፓርኩ አጎራባች ወረዳ አስተዳደር አካላትና የጊቤ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ ሠራተኞች ተሳትፈዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025