የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

የፖሊሲው ትግበራ ግብርናውን በማዘመን ምርታማነትን ይበልጥ ለማሳደግ ፋይዳው የላቀ ነው

Mar 13, 2025

IDOPRESS

ቡታጅራ ፤ መጋቢት 3/2017 (ኢዜአ) :-አዲሱ የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲ ትግበራ ዘርፉን በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ይበልጥ ለማሳደግ ፋይዳው የላቀ መሆኑ ተገለጸ።

ፖሊሲውን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማስተዋወቅን ዓላማ ያደረገ መድረክ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) እና የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋጤ ስርሞሎ በተገኙበት በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡


በዚህ ወቅት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ስሩር እንዳመለከቱት፤ ባለፉት ስድስት ዓመታት በስንዴ ልማት፣ በሌማት ትሩፋትና በሌሎችም ዘርፎች በርካታ ስኬቶች ማስመዝገብ ተችሏል፡፡

በዘርፉ እየተመዘገበ ያለውን ውጤት ለማጠናከርና የላቀ እመርታ ለማስመዝገብ እንደ አገር የተቀረጸው አዲሱ የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲ በክልሉ ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ፖሊሲው ግብርናን በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ይበልጥ ለማሳደግ ፋይዳ የላቀ መሆኑንም ገልጸዋል።

በመድረኩ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እየተሳተፉ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.