ቡኢ፤መጋቢት 3/2017 (ኢዜአ)፡- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የተገኘውን ውጤት ቀጣይነት ለማረጋገጥ በተቀናጀ መልኩ ሊሰራ እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) አስገነዘቡ ፡፡
"በላቀ ጥራትና ምርታማነት ወደ ሁለንተናዊ ብልፅግና ተምሳሌትነት" በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መድረክ ዛሬ በቡኢ ከተማ ተካሂዷል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንዳደገለጹት በክልሉ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በፈጠረው ምቹ መደላድል የኢንዱስትሪው ዘርፍ የተሻለ አፈጻጸምና መነቃቃት እያሳየ ይገኛል ፡፡
ዘርፉ ያሉበትን ችግሮች በአግባቡ በመለየትና በመፍታት ተወዳዳሪነትን እንዲላበስ የተደረጉ ጥረቶች መኖራቸውን ጠቅሰው "የቴክኖሎጂ አቅርቦትን በማሳደግ እንዲሁም ተኪ ምርት በአይነት፣ በጥራትና በብዛት በማምረት የውጭ ምንዛሬን ማዳን ተችሏል " ብለዋል ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ እየተመዘገቡ የመጡ ውጤቶችን ቀጣይነትና ዘላቂነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ አንስተው እንደ ክልል ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ማነቆ የሆኑ ችግሮችን በቁርጠኝነት መፍታት ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን አስገንዝበዋል።
በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ታምርት ፅህፈት ቤት የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ክላስተር አስተባባሪ አቶ መስፍን ንጉሴ "የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የዘርፉ ተግዳሮቶችን በመፍታት በርካታ ውጤቶች እየተመዘገበበት ይገኛል" ብለዋል፡፡
በዚህም ከ625 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች መልሰው እንዲያገግሙና ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱ ማድረግ መቻሉን አንስተው "ተወዳዳሪ የሆኑ ተኪ ምርቶችን በማምረት የገቢ ምንጭ ሆነዋል " ሲሉ አክልዋል፡፡
የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አባስ መሀሙድ (ዶ/ር) እንደገለፁት በክልሉ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች በሙሉ አቅም እንዲያመርቱ ለማስቻል የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል ፡፡
በክልሉ በተለያየ ደረጃ ፈቃድ የወሰዱ ከ530 በላይ ኢንዱስትሪዎች መኖራቸውን ጠቁመው ሁሉም በየዘርፋቸው አምርተው ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ የማጠናከርና የመደገፍ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በክልሉ በተለያዩ ዘርፎች ያሉትን ዕምቅ ሀብቶች በማስተዋወቅ አዲዲስ ባለሀብቶች ለመሳብ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ያነሱት አባስ (ዶ/ር) ለዚህም ከባለድርሻ አካላት ጋር በተቀናጀ መንገድ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና አልሚ ባለሀብቶች ተሳትፈዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025