ደብረ ብርሀን፤መጋቢት 5/2017(ኢዜአ) ፡-በአማራ ክልል እየተመረተ ያለውን ወተት ጥራቱ ተጠብቆ ለሸማቹ በቀጥታ እንዲደርስ የገበያ ትስስር እየተመቻቸ መሆኑን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ገለጸ።
በቢሮው የእንስሳት ተዋጽኦ ግብይት ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ክንዴ ለኢዜአ እንደተናገሩት፥ አርሶ አደሩ ወተትን በጥራትና በብዛት አምርቶ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚነቱን እንዲያሳድግ እየተሰራ ነው።
በበጀት ዓመቱ ውስጥ 185 ሚሊዮን ሊትር ወትት በማምረት ለገበያ ለማቅረብ ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን ጠቅሰው፥ከታቀደው ውስጥ እስካሁን ከ83 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሊትር በላይ ወተት በማምረት ለገበያ ማቅረብ መቻሉን ገልጸዋል።
ለገበያ የቀረበው የወተት ምርትም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከሁለት ሚሊዮን ሊትር በላይ ብልጫ እንዳለው ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
በክልሉ የሚመረተውን ወተት ጥራትና ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችል የግብይት ቁጥጥር ስራው በህግ ማዕቀፍ እንዲመራ ለማድረግ ቢሮው እየሰራ ነው ብለዋል።
የወተት የግብይት ማዕከላትን በከተሞች በማቋቋም ምርቱ ከአምራቹ በቀጥታ ለሸማቹ ማህበረሰብ እንዲደርስ የሚያገናኝ የገበያ ትስስር የማመቻቸት ተግባር እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህም የምርት ጥራት መፈተሻ መሳሪያን በመጠቀም ጭምር እንደሆነ አመልክተዋል።
ወተት የሚያቀነባብሩ ፋብሪካዎችን በዩኔኖች፣ህብረት ስራ ማህበራትና ባለሃብቶች በስፋት ለማቋቋም አስፈላጊው እገዛ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።
በደብረ ብርሃን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ የእስሳትና እንስሳት ተዋጽኦ ቡድን መሪ አቶ ዳዊት አሳምነው በበኩላቸው፥ ለሸማቹ የሚቀርብ የወተት ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ ነው ብለዋል።
ይህም በእንስሳት ጤና አጠባበቅ፣ አመጋገብና ንጽህና ላይ በማተኮር መሆኑን ገልጸዋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ የወተት ግብይት ህብረት ስራ ማህበር አባል አቶ ለገሰ በጋሻው በሰጡት አስተያየት፥በማህበር መደራጀታችን የእንስሳት መኖ፣ ክትባትና ህክምና በተፋጠነ መንገድ እንድናገኝ አስችሎናል ብለዋል።
በዚህም የወተት ምርታማነትን በማሳደግ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በወተት ምርት ግብይት ላይ የተጀመረው የጥራት ቁጥጥር ፍትሃዊ ግብይትና ተጠቃሚነት እንዲኖር የሚያስችል መሆኑን የተናገሩት ደግሞ ሌላው አባል አርሶ አደር ግዛቸው ሸዋዬ ናቸው።
እሳቸውም በየቀኑ የወተት ምርት ለማህበራቸው በማቅረብ በዓመት ከ250 ሺህ ብር በላይ የተጣራ ትርፍ እንደሚያገኙ ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025