የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

የምስራቅ አፍሪካ የአገር ውስጥ ገቢ ኮሚሽነሮችና ሚኒስትሮች ስብሰባ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው

Mar 15, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 05/2017(ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የአገር ውስጥ ገቢ ኮሚሽነሮችና ሚኒስትሮች ስብሰባ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ይገኛሉ።

በጉብኝቱ የምስራቅ አፍሪካ የገቢዎች ሚኒስትሮች፣ የጉምሩክ ኮሚሽነሮችና የስብሰባው ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች የአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከልን ጨምሮ በከተማዋ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን በተመለከተ ለጎብኚዎቹ ገለጻ እየሰጡ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.