አዲስ አበባ፤ መጋቢት 06/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ታዳጊዎችን በፈጠራና ቴክኖሎጂ ዕውቀት ለማብቃት ያላትን ቁርጠኝነት የአሜሪካ ኤምባሲ አደነቀ።
አሜሪካ የመጪው ዘመን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ መሪ ለሚሆኑት አፍሪካውያን ወጣቶች ድጋፍ እያደረገች መሆኗንም ጠቁመዋል።
በአሜሪካ ኤምባሲ የባህል ጉዳዮች ምክትል ኃላፊና በኢትዮጵያ የስፔስ ማዕከላት ዳይሬክተር ስትዋርት ዴቪስ እንደገለጹት፤ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግና ሂሳብ(ስቴም) አሜሪካ ድጋፍ ከምታደርግባቸው ዘርፎች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።
በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ባሉ ስድስት የ'ስቴም' ማዕከላት በ'ስቴም'፣ ሮቦቲክስና ሌሎች ቴክኖሎጂ ዘርፎች ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል።
የስቴም ማዕከላቱን ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በመቀሌ፣ ድሬዳዋና ጅማ መኖራቸውን ጠቁመው፤ በሃዋሳ ተጨማሪ ማዕከል ለመክፈት እየተሰራ ነው ብለዋል።
በኢትዮጵያ ታዳጊዎች በሮቦቲክስ፣ ቴክኖሎጂና ሌሎች የፈጠራ ሃሳቦችን ለማበልፀግ የሚያስችሉ ስራዎች መሰራታቸውን አድንቀዋል።
በየጊዜው ወደ ማዕከላቱ የሚመጡ ታዳጊ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር እያደገ መምጣቱን ጠቁመው፤ ይህም ታዳጊዎቹ ለመማርና ለመሻሻል ያላቸውን ፍላጎት የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ የሳይንስ ሙዚየምን ጨምሮ የታዳጊዎችን የፈጠራና ቴክኖሎጂ እውቀት ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ለዘርፉ ማደግ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።
አሜሪካም አፍሪካውያን በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላቸውን አቅም እንዲያወጡ ለማድረግ እገዛ እያደረገች መሆኗን ጠቁመዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025