አዲስ አበባ፤ መጋቢት 8/2017(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን በ2017 በጀት አመት ስድስት ወራት ሶስት ሺህ መብቶችን መመዝገቡን ገልጿል።
ባለሥልጣኑ ለቅጅና ተዛማጅ መብቶች፣ ለፓተንቶች(የግልጋሎት ሞዴሎችን ጨምሮ)፣ ለኢንዱስትሪያዊ ንድፎች እና ለንግድ ምልክቶች የመብት ጥብቃ ያደርጋል።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወልዱ ይመስል ለኢዜአ እንደገለፁት፤ ባለስልጣኑ በርካታ አመታት ማስቆጠሩን ተናግረዋል።
በእነዚህ አመታት በርካታ ስራዎች ቢያከናውንም በሚፈለገው ልክ እንዳልነበርም ጨምረው ገልፀዋል።
ለአብነትም እስከ 2015 ድረስ በዓመት በሁሉም መብቶች ጥቂት ምዝገባ ማከናወኑን ጠቅሰዋል።
ተቋሙ ባለፉት 20 አመታት 500 ፓተንት መመዝገቡን ተናግረው፤ ይህን ለማሻሻል የምዝገባ ስርዓቱ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን ገልፀዋል።
በዚህም በ2017 በጀት አመት ስድስት ወራት ሶስት ሺህ መብቶች መመዝገቡን ተናግረው፤ የቅጅና ተዛማጅ፣ ፓተንት እና የንግድ ምልክት መብቶችን መመዝገቡን ነው የተናገሩት።
አሁን ላይ ያሉ ጅምር ስራዎች አበረታች ቢሆኑም በሚፈለገው ደረጃ ላይ አለመድረሱንም ይገልጻሉ።
ይህም የሆነበት ምክንያት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚከናወኑ የምርምር ውጤቶችን ከማሳተም ባሻገር ፓተንት እንዲወጣባቸው ስለማይደረግ መሆኑን ጠቁመዋል።
በዚህም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያከናውኗቸውን የምርምር ስራዎች ከማሳተም ባሻገር ወደ ፓተንት እንዲያሻግሩ ጥሪ አቅርበዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025