አዲስ አበባ፤ መጋቢት 8/2017(ኢዜአ):- ሶስተኛው የአፍሪካ ማዕድን ፎረም ከሁለት ቀን በኋላ በአዲስ አበባ ይደረጋል።
ፎረሙ “የአፍሪካ የማዕድን ራዕይ ስኬቶች፣ ፈተናዎች እና ዕድሎች” በሚል መሪ ሀሳብ በአፍሪካ ሕብረት አካል በሆነው የአፍሪካ ማዕድናት ልማት ማዕከል የተዘጋጀ ነው።
ከመጋቢት 10 እስከ 12 በሚካሄደው ፎረም የህብረቱ አባል ሀገራት፣ የማዕድን ዘርፍ ተዋንያን፣ የልማት አጋሮች እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ይሳተፋሉ።
አፍሪካ የዓለምን 30 በመቶ የማዕድን ክምችት የያዘች ሲሆን የማዕድን ሀብቱ ለኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለኢንዱስትሪ መስፋፋትና የአረንጓዴ ኃይል ሽግግር ጠንካራ መሰረት መሆኑን ህብረቱ አመልክቷል።
ሶስተኛው የአፍሪካ ማዕድን ፎረም በማዕድን አስተዳደር፣ እሴት መጨመር እና ዘላቂነት ያሉ መዋቅራዊ ዕክሎች መፍታትና እድሎች መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ይመክራል።
በፎረሙ የማዕድን ቁፋሮን ስርዓትን ማዘመን፣ የካርቦን ልህቀትን መቀነስና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ማረጋገጥና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ላይ ውይይት ይደረጋል።
በማዕድን መስክ ያሉ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ የትኩረት መስኮችን ከአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና እና አጀንዳ 2063 ጋር አጣጥሞ በማስኬድ ጠንካራ አጋርነት መፍጠር ሌላኛው የፎረሙ አጀንዳ ነው።
ማዕከሉ የአፍሪካ የማዕድን ሀብቶች ለአህጉሪቷ ዘላቂ ልማትና ሁሉን አቀፍ እድገት ያላቸው አበርክቶ ማሳደግ ላይ እንደሚሰራ የህብረቱ መረጃ ያመለክታል።
ሁለተኛው የአፍሪካ የማዕድን ፎረም እ.አ.አ በ2022 በሩዋንዳ ኪጋሊ መካሄዱ የሚታወስ ነው።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025