ዲላ፤ መጋቢት 9/2017(ኢዜአ)፡- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዘንድሮ የበልግ እርሻ ከ642 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ታርሶ 46 ሺህ ሄክታሩ በዘር መሸፈኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
በክልሉ በመስኖ ለምቶ ከደረሰ ሰብል ከ11 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡም ተመላክቷል።
የቢሮው ምክትልና የእርሻ ልማት ዘርፍ ሃላፊ አቶ አድማሱ አወቀ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ከየካቲት እስከ ግንቦት ወር በሚከናወነው የበልግ እርሻ የተሻለ ምርት ለማምረት እየተሰራ ነው።
በበልግ ወቅት በቋሚ፣ በአዝዕርትና በሆርቲካልቸር ሰብሎች ከ848 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በማልማት ከ77 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ትግበራ መገባቱን ጠቅሰዋል።
እስካሁንም ከ642 ሺህ 300 ሄክታር በላይ መሬት መታረሱን ጠቅሰው ከዚህ ውስጥ 46 ሺህ ሄክታሩ በዘር መሸፈኑን አስረድተዋል።
የእርሻ ስራውን ውጤታማ ለማድረግ ለግብአት አቅርቦት ትኩረት መሰጠቱን ገልጸው፣ በአሁኑ ወቅት ለአርሶ አደሩ አስፈላጊው ማዳበሪያና ምርጥ ዘር እየተሰራጨ መሆኑን ተናግረዋል።
እንደ አቶ አድማሱ ገለጻ በተለይ በክልሉ ዋና ዋና ሰብሎች በቆሎ እና ማሽላ የአቅርቦት ውስንነት እንዳይገጥም በየደረጃው ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።
በክልሉ የሜካናይዜሽን እርሻን ለማስፋፋት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው፣ ለሜካናይዜሽን አመቺ በሆኑ የክልሉ አካባቢዎች 195 ትራክተሮችን በማሰማራት የእርሻ ስራውን የማገዝ ስራ እየተከናወነ ይግኛል ብለዋል።
አሁን ያለውን የዝናብ ስርጭትና የአየር ሁኔታን በአግባቡ በመጠቀም የበልግ አዝመራን ለማሳካት አመራሩን ጨምሮ በርብርብ እየተሰራ መሆኑን አቶ አድማሱ አንስተዋል።
በቋሚ ሰብሎች በተለይ በፍራፍሬና እንሰት ልማት የማሳ እንክብካቤን በማጠናከር ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑንም አቶ አድማሱ ጨምረው ገልጸዋል።
እንደሳቸው ገለጻ በክልሉ ሁሉንም የውሃ አመራጮች በመጠቀም 142ሺህ 563 ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ፣ በአትክልት፣ በስራስርና በተለያዩ ሰብሎች ለመሸፈን ተችሏል።
እስካሁንም ከ40ሺህ 588 ሄክታር በላይ የደረሰ ስብልን በማንሳት ከ11 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ተሰብስቦ ለገበያ መቅረቡን አስረድተዋል።
በበጋ መስኖ ለምቶ የደረሰ ምርት በኮምባይነር እና አርሶ አደሩን በማስተባበር በደቦ ለማንሳት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው፣ በክልሉ ሁሉም ዞኖች የበልግ እርሻን በኩታ ገጠም የእርሻ ዘዴ ታግዞ ለማከናወን የተጠናከር ክትትል እየተደረገ መሆኑንም አስረድተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025