አዲስ አበባ፤ መጋቢት 10/2017(ኢዜአ፦ ኢትዮጵያ ከጋምቢያ ለመጣ ልዑክ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ልምድ አካፈለች።
በጋምቢያ የማዕከላዊ ባንክ ተቀዳሚ ምክትል ገዥ አብዱላዮ ሲረህ ጃሎ(ዶ/ር) የተመራ ልዑካን ቡድን በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በመገኘት ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢነርጂ ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር) ጋር ተወያይቷል፡፡
ውይይቱም በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተሞክሮ ላይ ትኩረት የደረገ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።
ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ሀይል ከውሃ የማመንጨት የዳበረ ተሞክሮ እንዳላት አንስተው፤ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአፍሪካ በትልቅነቱም ሆነ፤ በፋይናንስ ምንጭና ከህዝባዊ ተሳትፎ አንጻር በርካታ ተሞክሮዎች የተገኘበት ትልቅ ፕሮጀክት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የህዳሴ ግድብ በመንግስት ቁርጠኝነትና በህዝቦች የነቃ ተሳትፎ በራስ የፋይናንስ አቅም የተገነባና የህዝቦችን አንድነት ያጠናከረ ታላቅ ፕሮጀክት ነው ብለዋል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንበታ እንዳይሳካ የተደረጉ ጥረቶችን በሙሉ በጥበብ በማለፍ ግድቡ ሀይል ማመንጨት ጀምሯል ብለዋል፡፡
ከታላቁ ህዳሴ ግድብ የድርድር ሂደቶች ጋር ተያይዞ ባደረጉት ገለጻ የአፍሪካን ጉዳዮች በአፍሪካውያን በሚል መርህ የድርድር ሂደቶች የተመሩበት አግባብ ትልቅ ማስተማሪያ ሆኗል በማለት ገልጸዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025