አዲስ አበባ፤ መጋቢት 11/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለሀገራዊ ስትራቴጂክ ፕሮጀክቶች ትኩረት በመስጠት በአፍሪካ ትልቁን አየር መንገድ ለመገንባት በርካታ ሥራዎች እያከናወነች መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ናቸው።
በማብራሪያቸውም፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአውሮፕላን ቁጥር፣ በመዳረሻ ብዛት ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገቡን ገልጸዋል፡፡
ከዚህም ባለፈ አየር መንገዶችን አስመርቆ ሥራ በማስጀመር እና የበረራ ድግግሞሽን በማሳደግ አገልግሎቱንና ትርፋማነቱን ጨምሯል ብለዋል፡፡
የዲዛይንና የፋይናንስ ጉዳዮች ሲጠናቀቁ ሥራው እንደሚጀመር ገልጸው፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በፋይናንስ አቅሙ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ የማይተናነስ ሀገራዊ ስትራቴጂክ ፕሮጀክት መሆኑን አንስተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ተጨማሪ መርከቦችን በማስገባት ሥራውን ለማዘመንና ትርፋማነቱን ለማረጋገጥ ጥረት እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
የባቡር ትራንስፖርት አፈፃፀም ከአምናው ወቅት ጋር ሲነፃፀር በእጅጉ መጨመሩንና የዲጂታል ግብይት ከእጥፍ በላይ ማደጉን ተናግረዋል፡፡
በቅርቡ የተጀመረው የካፒታል ገበያ ለአምስት ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ፈቃድ መስጠቱን አንስተው፤ የዲጂታል ግብይቱና የንግድ ስርዓቱ በዚያው ልክ እየዘመነ የሚሄድበትን እድል ፈጥሯል ብለዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025