አዲስ አበባ፤ መጋቢት 11/2017(ኢዜአ)፡- የኮሪደር ልማት ከዛሬ ባሻገር ቀጣዩ ትውልድን መሰረት ያደረገ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።
በማብራሪያቸውም የኮሪደር ልማት ከዛሬ ባሻገር ቀጣዩ ትውልድን መሰረት ያደረገ ነው ብለዋል።
በአዲስ አበባ ብቻ በኮሪደር ልማት አማካኝነት ከ200 ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ መሰራቱን ጠቁመው ሰፋፊ የእግረኛ መንገዶችም ተከናውነዋል ነው ያሉት።
በኮሪደር ልማቱ ለተነሱ ዜጎችም በቂ ካሳ ተከፍሏል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስካሁን ባለው ሂደትም ከ17 ቢሊዮን ብር በላይ ካሳ ተከፍሏል ብለዋል።
በሁሉም የክልል ከተሞችም አስደማሚ ስራ እየተከናወነ ነው፤ ለአብነትም በሐረር ከተማ በዜጎች ተሳትፎ የተከናወነው ስራ ለሀሉም ከተሞች ምሳሌ የሚሆን መሆኑን ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025