አዲስ አበባ፤ መጋቢት 18/2017(ኢዜአ)፡- ወጣቱ በሳል የሆነ የማኀበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን በመከተል እንደሚገባው ኢዜአ ያነጋገራቸው ወጣቶች ገለጹ።
ማህበራዊ ሚዲያ የሰው ልጅን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ እንዲሁም አኗኗር ቀላል እያደረገው መጥቷል።
በአዲስ አበባ ኢዜአ ያነጋገራቸው ወጣቶች ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚወጡ መረጃዎችን በሙሉ ከመውሰድ ይልቅ አጣርቶ መጠቀም ይገባል ይላሉ።
ወጣት ህይወት አምባው እንዳለችው፤ አንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የተለያየ ዓላማን በመያዝ ሀሰተኛ መረጃዎችን ሲያሰራጩ ይስተዋላል።
በመሆኑም መረጃዎቹን ከመጠቀም በፊት ትክክለኛነታቸውን ማጣራት ይገባል ብላለች።
ወጣት ህይወት በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቀቁ መረጃዎች ምንጫቸው ከየት ነው? ትክክለኛነቱስ ምን ያህል ነው? የሚለውን ማጤን ይገባልም ስትል ትመክራለች።
ወጣቶች ትክክለኛ መረጃዎችን ከትክክለኛ ምንጮች በመውሰድ ራሳችንን ከሀሰተኛ መረጃ ከመጠበቅ ባለፈ ለህዝቦች አብሮነት መስራት አለብን ብላለች።
ወጣቶች ማህበራዊ ሚዲያን ለምን ዓላማ ነው የምንጠቀመው የሚለውን ቆም ብለን ልናስብ ይገባል ያለው ደግሞ ወጣት ሃይለማሪያም ተሰማ ነው።
የወጣቱ ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ብስለት የተሞላበት ሊሆን እንደሚገባና ሚዲያውን ለበጎ ነገር መጠቀም ይገባል ብሏል።
በማህበራዊ ሚዲያ በርካታ ተከታዮችን ማፍራት መቻሉን የጠቀሰው ወጣት በረከት ከበደ በበኩሉ በማህበራዊ ሚዲያው የሚያስተላልፈውን መልዕክት ለሀገርና ለሕዝብ ምን ያህል ይጠቅማል የሚለውን የመመዘን ልምድ እንዳለው ገልጿል።
በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ላይ ያለውን ልምድ ለወጣቶች በማካፈል የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ መሆኑንም ነው የጠቆመው።
ወጣት መንበረ መልኬ በበኩሉ ወጣቱ ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ለሀገር የሚጠቅም ገንቢ ሚና እንዲጫወት ግንዛቤን የማስፋት ሥራ ሊጠናከር ይገባል ብሏል።
ለዚህም ባለድርሻ አካላት የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን መስጠት ላይ በልዩ ትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ በመጠቆም።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025