የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

በዲጅታል ቴክኖሎጂ የተደገፈ የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥ በተጠናከረ መልኩ ሊቀጥል ይገባል- ቋሚ ኮሚቴው

Apr 3, 2025

IDOPRESS

ባህርዳር ፤መጋቢት 24/2017(ኢዜአ)፡- በዲጅታል ቴክኖሎጂ የተደገፈ የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥ በተጠናከረ መልኩ ሊቀጥል እንደሚገባ በህዝብ የተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስገነዘበ።

በህዝብ የተወካዮች ምክር ቤት የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባከናወናቸው ተግባራት ላይ ከዳኞችና ተገልጋዮች ጋር በዛሬው እለት ውይይት አካሂዷል።


የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወይዘሮ እፀገነት መንግስቱ፤ በዲጅታል ቴክኖሎጂ በመታገዝ እየተሰጠ ያለው የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥ የሚበረታታ መሆኑን አንስተው በተጠናከረ መልኩ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

የፍትህ ዘርፉን ፈጣን፣ ግልጽ፣ ተአማኒና ሚዛናዊነቱ የተጠበቀ እንዲሆን በሚደረገው ጥረት የድጂታል አሰራሮችን ማስፋትና ማጠናከር ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህ ረገድ በአማራ ክልል የተጀመሩ ጥረቶችና እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን ጠቅሰው ይህም ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል።


የቋሚ ኮሚቴው ጉብኝትም የሀገሪቱን የፍትህ ትራንስፎርሜሽን መርሃ-ግብር አተገባበር ለመገምገም መሆኑን ገልጸዋል።

የዳኝነት አካላት የለውጥ ፍኖተ ካርታ አፈጻጸም ለመመልከትና አፈጻጸሙን ከተገልጋዩ በመረዳት ግብረመልሶችን በመቀበል ለቀጣይ ስራ አቅጣጫ ለማመላከት መሆኑንም አስረድተዋል።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህንጻ የእድሳት ሂደት በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መመልከታቸውን ጠቁመው ይህም ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር የሚያስችል ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.