የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

ኢትዮጵያ በ177ኛው የፋኦ የካውንስል ስብሰባ እየተሳተፈች ነው

Apr 8, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 29/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ዛሬ በጣልያን ሮም በተጀመረው 177ኛው የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት(ፋኦ) የካውንስል ስብሰባ እየተሳተፈች ነው።

በጣልያን የኢትዮጵያ አምባሳደር እና በዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት፣ በዓለም የምግብ ፕሮግራም እና የዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ የኢትዮጵያ ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ደሚቱ ሃምቢሳ በስብሰባው ላይ ተገኝተዋል።

አምባሳደር ደሚቱ ሀገራት የምግብ ዋስትናቸውን ለማረጋገጥ እያከናወኑ ያሉትን ውጤታማ ስራና በዚሁ ረገድ እያጋጠማቸው ያለውን ፈተና አስመልክተው አፍሪካን ወክለው ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

በስብሰባው ፋኦ በስትራቴጂክ እቅዱ ላይ በመወያየት አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

ሀገራት የምግብ ዋስትናቸውን ለማረጋገጥ እያጋጠማቸው ያለው ፈተና እና መፍትሄዎቻቸው እንዲሁም ድንገተኛ አደጋ በሚያጋጥማቸው ወቅት አፋጣኝ ምላሽ መስጠት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ይመክራል።

ስብሰባው እስከ ሚያዚያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.