አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30/2017(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት የከተማዋን ውበት ያሳየና የቱሪዝም መስህብነቷን ያሳደገ መሆኑን ኢዜአ ያነጋገራቸው የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችና ግለሰቦች ገለጹ፡፡
የኮሪደር ልማት ስራዎችን በባለቤትነት መጠበቅና መንከባከብ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
በአዲስ አበባ የተገነቡ እና እየተገነቡ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎች ከተማዋን እንደ ስሟ ውብና ሳቢ በማድረግ ተመራጭነቷን ያሳደገ ነው፡፡
የከተማዋ የኮሪደር ልማት የነዋሪዎችን የአኗኗር ዘይቤ ያሻሻለ፣ ከተማዋን የሚመጥን፣ ዘመኑን የዋጀ የመሰረተ ልማት አቅርቦት የጨመረና የከተማዋን ገጽታ የቀየረ ፕሮጀክት ነው፡፡
ኢዜአ ያነጋገራቸው የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች የኮሪደር ልማት ስራ የከተማዋን የዕድገት ደረጃ ይበልጥ የሚያሣልጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል መንሱር ጀማል እንተገለጸው በሀገር ደረጃ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ዜጎች ምቹና ዘመናዊ የሆነ ከባቢ እንዲኖራቸው ያስቻለ፤ የዜጎችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ያሳደገ ነው፡፡
በመዲናዋ የተከናወኑና እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችም አዲስ አበባ እንደስሟ ውብ፣ ጽዱና ደረጃዋን የጠበቀች እንድትሆን ማስቻሉን ገልጿል፡፡
መንግስት የዜጎችን የልማት ጥያቄ ለመመለስና የሀገርን ገጽታ ለመገንባት የሚያከናውናቸው ተግባራት ከግብ እንዲደርሱ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ብሏል፡፡
አርቲስት ሙሉነህ ዘለቀ በበኩሉ በሀገር ደረጃ እየተተገበሩ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎች የቱሪስት መዳረሻነትን ያሳደጉ መሆናቸውን ተናግሯል፡፡
በከተማዋ በተለያዩ ቦታዎች ላይ የተገነቡ የህጻናት መጫወቻዎች፣ የመዝናኛ እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ጨምሮ ሌሎች ልማቶች መጪውን ትውልድ የሚመጥኑ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎችን የመለሱ መሆናቸውን ገልጿል፡፡
የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎችን በባለቤትነት መጠበቅና መንከባከብ እንደሚገባም ጠቁሟል፡፡
የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በከተማዋ የሚከናወኑ የልማት ስራዎችን ለረጅም ዓመታት አገልግሎት እንዲሰጡ ሁሉም አካል መጠበቅና መንከባከብ እንደሚገባው የገለጸው ደግሞ አርቲስት ኤልያስ ተባባል ነው፡፡
የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ሌሎችም ከተሞች ልምድ እየቀሰሙበት የሚገኝ መልካም ተሞክሮ ነው።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025