አዲስ አበባ፤ መጋቢት 30/2017(ኢዜአ)፦ የአፍሪካውያን የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ላይ እርስ በእርስ ያላቸውን የንግድ ልውውጥ ይበልጥ ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።
በምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ አገራት የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) ሥር የሚገኘው የአፍሪካ ቆዳና ቆዳ ውጤቶች ኢንስቲትዩት ያዘጋጀውና የቆዳ ውጤቶች ገበያ ትስስር ላይ ያተኮረ መድረክ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
በዚሁ ጊዜ አፍሪካ ያላትን የእንሰሳት ሃብት የበለጠ ጥቅም ላይ ለማዋል በቆዳና ቆዳ ውጤቶች ላይ የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎችን አቅም ማሳደግ ተገቢ መሆኑ ተነስቷል።
አፍሪካውያን በዘርፉ ያላቸው የንግድ ልውውጥ ዝቅተኛ በመሆኑ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ለዚህ መፍትሄ እንደሚሆን ተመላክቷል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ያስሚን ወሀብረቢ አህጉሪቷ ያላትን እምቅ የእንሰሳት ሃብት የበለጠ ለመጠቀም የእሴት ሰንሰለቱን ማሳደግ ይገባል ብለዋል።
የቆዳና ቆዳ ውጤቶችን በጥራትና ተወዳዳሪነት ለማሳደግም ለአምራቾች የተለያዩ የቴክኒክ ድጋፎች እየደረጉ ነው ብለዋል።
በአፍሪካ አገራት መካከል ያለውን የእርስ በእርስ የንግድ ልውውጥ የበለጠ በማሳደግ ከዘርፉ የተሻለ ገቢ ለማግኘትም የተጀመሩ ስራዎች መኖራቸውን ጠቅሰዋል።
የአፍሪካ ቆዳና ቆዳ ውጤቶች ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኒኮላስ ሙዱንግዊ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል እየፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢንዱስትሪውን በቴክኖሎጂ በማዘመንና እሴት በመጨመር አለምአቀፍ ተወዳዳሪ ለማድረግም ተቋማቸው ለአገራት የቴክኒክ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
የአፍሪካ አገራት የንግድ ልውውጣቸውን በማሳደግ ከዘርፉ የተሻለ ገቢ እንዲያገኙ በትብብር መስራት እንደሚገባም አንስተዋል።
የኢትዮጵያ አምራቾች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሚልኬሳ ጃገማ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የአምራች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ በቴክኖሎጂ በመደገፍ ጥራቱን የጠበቀ የቆዳና ቆዳ ውጤቶችን ለማምረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
መንግስት የቆዳ ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ ካለው ፍላጎትም ስትራቴጂ ከመቅረጽ ባለፈ ለአምራቹ የተለያዩ ማበረታቻዎችን እያደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ከእነዚህ ውስጥ ገነት አበጋዝና እጅጋየሁ ደግፌ ምርቶቻቸውን ከአገር ውስጥ ባለፈ ለተለያዩ የአፍሪካ አገራት የማቅረብ ፍላጎት እንዳላቸው አንስተዋል።
የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራ ለዚህ ምቹ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ተናግርዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025