አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 2 /2017(ኢዜአ)፦ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በማስፋፋት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ የአገልግሎት አሠጣጥን የማዘመን ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጠል የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
የትራንስፖርት ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የጭነት ትራንስፖርትን ለመቋጣጠርና ለማስተዳደር የሚያስችል የተቀናጀ የትራንስፖርት አስተዳደር (IFTMS) ሲስተም አስጀምሯል።
የትራንስፖርት ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በማስጀመሪያ ስነ-ስርአቱ ላይ እንደገለጹት፥ በትራንስፖርት ዘርፍ የሚሰጠውን የአገልግሎት አሰጣጥ ይበልጥ ፈጣንና ቀልጣፋ ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ የሪፎርም ስራዎች ተሰርተዋል፡፡
ዛሬ የተመረቀው ሲስተም የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎትን በማዘመን እና በማቀላጠፍ በኩል ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወትም ገልጸዋል፡፡
በዘርፉ የሚሰጡ የአገልግሎት አሰጣጦችን ዲጂታል ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አንስተው፤ ሌሎች በዘርፉ ተግባራዊ የሚደረጉ ቴክኖሎጂዎችም በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገቡ ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ የትራንስፖርት አገልግሎትን የሚያዘምነው ሲስተም በተባለው ጊዜ መጠናቀቁን አስታውቀዋል።
ኢንስቲትዩቱ የአገልግሎት አሰጣጦችን የሚያቀላጥፉና ችግሮችን የሚፈቱ ቴክኖሎጂዎችን የማልማቱን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ተወዳዳሪ የሚያደርጋትን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አቅም የመገንባት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
የተመረቀው ሲስተም የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያበለጸገው መሆኑ ተገልጿል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025