አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 2/2017(ኢዜአ):-የኢትዮጵያ ነጋዴ ሴቶች ማህበር የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የጀመራቸውን አበረታች ስራዎች አጠናክሮ እንዲቀጥል የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ትስስርና ወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ያስሚን ወሀብረቢ አሳሰቡ።
የኢትዮጵያ ነጋዴ ሴቶች ማህበር ዕቅድ አፈፃፀምና ቀጣይ ስራዎች ላይ ዛሬ ውይይት ተካሂዷል።
ማህበሩ የካቲት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ አዲስ የማህበሩን ፕሬዝዳንትና 11 የቦርድ አባላትን ምርጫ ማካሄዱ የሚታወስ ነው።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ትስስርና ወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ያስሚን ወሀብረቢ ከጠቅላላ ጉባኤው በኋላ በተከናወኑ ስራዎች ዙሪያ ከማህበሩ አመራሮችና ከቦርዱ አባላት ጋር ተወያይተዋል።
ሚኒስትር ዴኤታዋ ማህበሩ ሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ባሳተፈ መልኩ የኢትዮጵያን ነጋዴ ሴቶች ለማብቃትና በንግዱ ዘርፍ በሴት ነጋዴዎች ላይ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የሚያስችል ነው ብለዋል።
ማህበሩ ባለፉት ጥቂት ወራት አበረታች ስራዎች ማከናወኑን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታዋ በኢትዮጵያ ለሚካሄደው የኮሜሳ የሴት ነጋዴዎች የቢዝነስ ኮንፍረንስና ኤግዚቢሽን የዝግጅት ስራ በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አመልክተዋል።
በቀጣይም በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ተደራሽነትን በማስፋትና ገቢ የሚያመነጩ ስራዎችን በማከናወን የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ ነጋዴ ሴቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ወይዘሮ በረከት ወርቁ በማህበሩ የተከናወኑ ስራዎችን አስመልክቶ ማብራሪያ መስጠታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025