አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 2/2017 (ኢዜአ):-በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ 2025 ከፍተኛ የቢዝነስ ፎረም በመጪው ግንቦት 4 እና 5 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገለጸ።
ፎረሙን በተመለከተ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) እና የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) እንደተናገሩት፥ የቢዝነስ ፎረሙ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ በገንዘብ ሚኒስቴር እና በአጋር የልማት ድርጅቶች የተዘጋጀ ነው።
ለ3ኛ ጊዜ የሚካሄደው በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ የቢዝነስ ፎረም ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ተቀዳሚ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ከማድረግ ባለፈ ዘላቂና ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገት ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ገልፀዋል።
አዳዲስ ኢንቨስትመንትን መሳብ፣መንግስት ለዘርፉ የሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት ማሳየት እና አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ ማሻሻያዎችን ማሳወቅ የፎረሙ ዓላማ ነው ብለዋል።
በፎረሙ የዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ ታዋቂ ኩባንያዎች፣የንግዱ ማህበረሰብ መሪዎች፣የፖሊሲ አውጪዎች፣አማካሪዎች እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ እንደሚሳተፉም ጠቁመዋል።በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ 2025 የቢዝነስ ፎረም ግንቦት 4 እና 5 በአዲስ አበባ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 2/2017 (ኢዜአ):-በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ 2025 ከፍተኛ የቢዝነስ ፎረም በመጪው ግንቦት 4 እና 5 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገለጸ።
ፎረሙን በተመለከተ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) እና የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) እንደተናገሩት፥ የቢዝነስ ፎረሙ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ በገንዘብ ሚኒስቴር እና በአጋር የልማት ድርጅቶች የተዘጋጀ ነው።
ለ3ኛ ጊዜ የሚካሄደው በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ የቢዝነስ ፎረም ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ተቀዳሚ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ከማድረግ ባለፈ ዘላቂና ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገት ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ገልፀዋል።
አዳዲስ ኢንቨስትመንትን መሳብ፣መንግስት ለዘርፉ የሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት ማሳየት እና አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ ማሻሻያዎችን ማሳወቅ የፎረሙ ዓላማ ነው ብለዋል።
በፎረሙ የዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ ታዋቂ ኩባንያዎች፣የንግዱ ማህበረሰብ መሪዎች፣የፖሊሲ አውጪዎች፣አማካሪዎች እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ እንደሚሳተፉም ጠቁመዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025