አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 9/2017(ኢዜአ)፡- በውጭ ምንዛሬ ጨረታው አንድ ዶላር በአማካይ 131 ነጥብ 4961 ብር መሸጡን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገለጸ።
ባንኩ ዛሬ ያደረገውን የ70 ሚሊዮን ዶላር ጨረታ ውጤት ይፋ አድርጓል።
አንድ ዶላር በአማካይ በ131 ነጥብ 4961 ብር መሸጡንና በጨረታው ላይ የተሳተፉ 26 ባንኮች የውጭ ምንዛሬውን መውሰዳቸውን ገልጿል።
በዛሬው ጨረታ በተሸጠው ዶላር የባንኮቹን 96 በመቶ የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት/ጥያቄ በአጥጋቢ ሁኔታ ምላሽ መስጠት መቻሉን አመልክቷል።
ብሔራዊ ባንክ ቀጣይ የውጭ ምንዛሬ ጨረታውን ከሁለት ሳምንት በኋላ ያካሂዳል።
ባንኩ ጨረታው የሚያካሂድበት ቀን እና ሰዓት ጨረታው ከመካሄዱ ከአንድ ቀን በፊት አስቀድሞ እንደሚያሳውቅም ገልጿል።
ጨረታው በማዕከላዊ ባንክ እየተከማቸ ካለው የውጭ ምንዛሪ የተወሰነውን መጠን ለግሉ ዘርፍ ለማቅረብና የባንኩን የገንዘብ ፖሊሲ ዓላማ ለማሳካት እንደሚረዳ ተገልጿል።
በተጨማሪም ጨረታው የውጭ ምንዛሪ ገበያን ለማረጋጋትና ሪፎርሙ ከተጀመረ ወዲህ መሻሻል እያሳየ የመጣውን የውጭ ክፍያ ሚዛን በይበልጥ ለማጠናከር እንደሚያግዝም ነው ባንኩ ያመለከተው።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025