አሶሳ፤ ሚያዝያ 10/2017(ኢዜአ):- በአሶሳ ከተማ ለትንሳዔ በዓል የተሻለ የፍጆታ ቁሳቁስና የእርድ እንስሳት አቅርቦት መኖሩን ሸማቾች እና ነጋዴዎች ተናገሩ።
ኢዜአ የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአሶሳ ከተማ ያለውን የግብይት ሁኔታ ተዘዋውሮ ተመልክቷል።
በወቅቱ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ሸማቾች እና ነጋዴዎች እንደተናገሩት የፍጆታ ዕቃዎች እና የቁም እንስሳት አቅርቦት በበቂ ሁኔታ እንዳለ ገልጸዋል።
ዱቄት፣ ዘይት እና ሌሎች ለበዓል ፍጆታ የሚውሉ ዕቃዎችን ሲሸምቱ ያገኘናቸው ወይዘሮ ሙሉ ዓለሙ እንዳሉት በዓልን ምክንያት በማድረግ የተሻለ አቅርቦት አለ ብለዋል።
ይለፉ አበዛ የተባሉ የአትክልት እና ፍራፍሬ ነጋዴ በበኩላቸው ሽንኩርት በአካባቢው በስፋት በመመረቱ አቅርቦት ላይ ችግር እንደሌለ ጠቁመዋል።
በተመሳሳይ የቁም እንስሳት ግብይት አቅርቦትም በተሻለ ሁኔታ መኖሩንና መጠነኛ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን ሸማቾች ተናግረዋል።
በአሶሳ ከተማ የቁም እንስሳት ገበያ ማዕከል ያገኘናቸው ሸማች አቶ ስሜነህ ተፈራ የእርድ ሰንጋዎች ከሌላው ጊዜ በተሻለ መግባቱንና ሰው እንደየፍላጎቱ ግብይት እየፈጸመ መሆኑን አንስተዋል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አስር ኢብራሂም ነጋዴዎች የፍጆታ ዕቃዎችን በበቂ ሁኔታ እንዲያቀርቡ የቅድመ ዝግጅት ስራ መከናወኑን ተናግረዋል።
ህብረተሰቡ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በቀጥታ ከአምራቹ እንዲያገኝ በማድረግ የበዓል ገበያው የተረጋጋ እንዲሆን እየተሰራ ነው ብለዋል።
በቁም እንስሳት አቅርቦትና ፍላጎትን ለማጣጣም በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች በእርባታ እና በማድለብ ስራ የተሰማሩ አካላት ምርታቸውን ወደ ገበያ እንዲያቀርቡ ተደርጓል ነው ያሉት።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025