አዲስ አበባ፤ሚያዚያ 14/2017(ኢዜአ)፦በመዲናዋ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 124 የተለያዩ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገለጸ።
የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የፕሮጀክቶች ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክተር ብሩክ ተሆነ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ በመዲናዋ በርካታ ኢንቨስትመንትን የሚያበረታቱ የልማት ስራዎች ተከናውነዋል።
በመዲናዋ ባለፉት ጥቂት አመታት የተገነቡ የኮሪደር፣ የቱሪዝም መሰረተ ልማቶችና መዳረሻዎች እንዲሁም ሌሎች የልማት ስራዎች ኢንቨስትመንቱ እንዲያድግ እያስቻሉ ነው ብለዋል።
በከተማዋ ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረ በመሆኑም በተለይ በቱሪዝምና ሌሎች የአገልግሎት ዘርፎች ለመሰማራት በርካታ ባለሀብቶች ጥያቄ እያቀረቡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኮሚሽኑ ይህን ታሳቢ በማድረግ የኢንቨስትመንት ፍቃድ በተቀላጠፈ ሁኔታ ከመስጠት በተጨማሪ ፍቃድ የወሰዱ ባለሀብቶች በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገቡ ድጋፍና ክትትል እያደረገ መሆኑን አንስተዋል።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት በኮንስትራክሽን፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በአይሲቲ፣ በማኑፋክቸሪንግና በአገልግሎት ዘርፎች 124 ፕሮጀክቶች ወደ ስራ መግባታቸውን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
ፕሮጀክቶቹ ከአስር ሺህ በላይ ለሆኑ ነዋሪዎች የስራ እድል መፍጠራቸውን ተናግረዋል፡፡
የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በፍጥነት ወደ ተግባር መግባት ለከተማዋ ኢኮኖሚ ትልቅ ሚና እየተወጣ መሆኑንም አንስተዋል።
እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፥ኮሚሽኑ አገልግሎቱን ለማዘመን ዲጂታላይዜሽን ላይ ውጤታማ ተግባራትን በማከናወን የኢንቨስትመንት ጉዳዮችን በቀላሉ በኦንላይን መፈጸም እንዲቻል አድርጓል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን በማንሳት፥ ባለሀብቶች በተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025