የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በመዲናዋ በፍጥነትና በጥራት የተከናወኑ የልማት ስራዎች በፕሮጀክት አፈፃፀም ልምድ የሚወሰድባቸው ናቸው - የተቋማት የሥራ ኃላፊዎች

Apr 24, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 15/2017(ኢዜአ)፦ በፍጥነትና በጥራት የተከናወኑ የልማት ስራዎች በፕሮጀክት አፈፃፀም ልምድ የሚወሰድባቸው መሆናቸውን በአዲስ አበባ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን የጎበኙ የተለያዩ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ገለፁ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስተባባሪነት የገንዘብ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት፤ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግና በስሩ ያሉ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በመዲናዋ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝቷል።

ከጎበኟቸው የልማት ስራዎች መካከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ትላንት የተመረቀው የካዛንቺስ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል፣ የእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል፣ የገላን ጉራ የተቀናጀ የመኖሪያና የልማት መንደር እንዲሁም የጫካ ፕሮጀክት ይገኙበታል።


በዚሁ ጊዜ ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት ኑሪ ሁሴን በመዲናዋ የተከናወኑ የልማት ስራዎች የከተማዋን ውበት ከማጉላት ባሻገር የዜጎችን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ መሆናቸውን መገንዘባቸውን ተናግረዋል።

እንዲሁም አዲስ የስራ ባህልን ያሳደገ ልማት እንደሆነ ጠቅሰው፤ ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ማከናወን እንደሚቻል ትምህርት የሚወሰድበት ነው ብለዋል።


የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ምክትል ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ቤዛዊት ግርማ በበኩላቸው የልማት ስራዎቹ ፕሮጀክቶች በአመራር ቁርጠኝነት በፍጥነትና በጥራት እንደሚጠናቀቁ ያረጋገጡ ናቸው ሲሉ ገልጸዋል።

ኮርፖሬሽኑ ከዚህ ልምድ በመውሰድ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜ እና ሀብት ለማጠናቀቅ እንደሚሰራም ተናግረዋል።


የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ምክትል ስራ አስፈፃሚ ደመረ አሰፋ የልማት ስራዎቹ መዲናዋን ከማስዋብ ባሻገር ትምህርት በመውሰድ በተቋማቸው የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ገድብ ለማጠናቀቅ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።


በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የግብርና እና የአግሮ ፕሮሰሲንግ የፖርትፎሊዮ ዳይሬክተር አስማ ረዲ የልማት ስራዎቹ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ተጠቃሚ ያደረጉ ናቸው ብለዋል።

የስራ ባህል በማሳደግ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት እና በጥራት ለማጠናቀቅ የተደረጉ ጥረቶች የሚደነቁ እና ትምህርት የሚወሰድባቸው መሆናቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.