የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በካዛንቺስ የኮሪደር እና መልሶ ማልማት ስራ ላይ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላትን አመሰገኑ

Apr 24, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16/2017(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በካዛንቺስ የኮሪደር እና መልሶ ማልማት ስራ ላይ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላትን አመስግነዋል።


ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ትላንት ማምሻውን በካዛንቺስ ኮሪደር እና መልሶ ማልማት ስራ ላይ ሃገር የማበልፀግ ራእያችንን በመጋራት በርካታ እንቅልፍ አልባ ሌሊቶችን፣ እረፍት አልባ የስራ መርሃግብር በማሳለፍ አብረውን ለሰሩ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎች፣ አመራሮች፣ ሰራተኞች እና ተቋማትን አመስግነናል ብለዋል።


ከእነዚህም መካከል ማሽኖቻቸውን በነጻ ለዚህ ስራ ያዋሱ ባለሃብቶችን፣ ስራ ወስደው በፍጥነትና በጥራት ፕሮጀክቶችን በጊዜ በማጠናቀቅ ያስረከቡ ኮንትራክተሮች እና አማካሪዎችን፣ ይህን ስራ ከጅማሮ እስከ ፍጻሜ በፍጹም ታታሪነት እና ቅንነት ያስተባበሩ የከተማችን አመራሮችን፣ የግል የመንግስትና የፌደራል ተቋማትን እንዲሁም የህንጻ ባለንብረቶችን ራዕያችንን በመጋራት ሃገር በመገንባት ስራችን ላበረከቱት ጉልህ አስተዋፅዖ ሁሉ በራሴ እና በነዋሪዎቻችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ ሲሉም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.