አሶሳ፤ ሚያዝያ 23/2017(ኢዜአ):- በአሶሳ ከተማ የተካሄደው ክልላዊ የክህሎትና የቴክኖሎጂ ውድድር የተሻለ ተሞክሮ እንዳገኙበት የውድድሩ ተሳታፊዎች ተናገሩ።
"ብሩህ አዕምሮዎች፤ በቴክኒክ የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ሃሳብ ለስድስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው ክልላዊ የክህሎት፣ የቴክኖሎጂ እና ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር ዛሬ ተጠናቋል።
የክህሎት፣ የቴክኖሎጂ እና ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድሩ ላይ የተሳተፉ ተወዳዳሪዎች እንደገለፁት ውድድሩ የቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች ያሰለጠኑት የሰው ሀይል በተግባር የታገዘ መሆኑን ያመላከተ ነው።
ከተወዳዳሪዎቹ መካከል ከካማሽ ቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጅ የመጣው ሰልጣኝ አዲሱ ተሰማ በዳታ ቤዝ አስተዳደር ውድድር ሁለተኛ መውጣቱን ገልፆ ከሌሎች ተወዳዳሪዎች ተጨማሪ ክህሎት እንዳገኘ ገልጿል።
እንደነዚህ አይነት ውድድሮችን ማዘጋጀት የቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች ሰልጣኞችን የፈጠራ አቅም ለማጠናከር ያግዛል ብሏል።
ሌላዋ በአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሰልጣኝ እና በኢንዱስትሪያል እና ኤሌክትሪካል ዘርፍ የተወዳደረችው ነፃነት ፉፋ ውድድሩ አዳዲስ የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ስራዎች እንዲተዋወቁ ዕድል መፍጠሩን ገልፃለች።
የቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት ምቹ የሥራ ቦታ እንዲፈጥሩ ለማድረግ እንዲሁም የአካባቢውን ፀጋ ጥቅም ላይ ለማዋል ያለመ ተግባራዊ ጥናት ይዘው በቡድን መወዳደራቸውን የገለፀው ከማንቡክ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የመጣው ኢንስትራክተር ፍሬው ከበደ ነው።
በቀጣይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚደረገው ውድድር የተሻለ የፈጠራ እና የክህሎት ስራ ለማዳበር ዝግጁ መሆኑን በመጠቆም።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱሰላም ሸንገል በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ እንዳሉት በክልሉ በመፍጠር እና በማሸጋገር የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል።
ኮሌጆች ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ እንዲሁም ገቢ ምርቶችን የሚተኩ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እያፈለቁ መሆኑን ጠቁመዋል።
ለአብነትም የአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአሶሳ ከተማ እየተከናወነ ላለው የኮሪደር ልማት የቴራዞ ምርት በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በውድድሩ አሸናፊ የሆኑ ሰልጣኞች እና አሰልጣኞች በቀጣይ ሳምንት በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው ውድድር እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
ውድድሩ በአውቶ መካኒክ፣ በኤሌክትሪክ ስራ፣ በኮንስትራክሽን፣ በእንጨት ስራ እና በአጠቃላይ በስምንት የሙያ መስኮች የተደረገ ሲሆን ለአሸናፊዎቹ የዋንጫና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025