አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 24/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በክህሎት ልማት ሁለተኛውን የአርበኝነት ምዕራፍ መጀመሯን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ።
ኢትዮ ክህሎት አራተኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር "ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ሃሳብ ከሚያዚያ 27 እስከ ግንቦት 2 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተገልጿል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል መርኃ ግብሩን በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሃን ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።
ሚኒስትሯ በመግለጫቸው፤ ኢትዮ ክህሎት ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር የስልጠና ጥራትን ለማረጋገጥ በየሁለት ዓመቱ የሚካሄድ መሆኑን ተናግረዋል።
መርኃ ግብሩ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ሲካሄድ በቆየው ውድድር አሸናፊ የሆኑ ወጣቶች የሚሳተፉበት የክህሎትና የቴክኖሎጂ ውድድር መሆኑን አስታውቀዋል።
የክህሎት ውድድሩ ከኢትዮጵያ ፍላጎት ጋር የሚጣጣሙ እና ከገበያው ፍላጎት ጋር የሚያስተሳስሩ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎች ላይ የሚያተኩር መሆኑን ጠቁመዋል።
ውድድሩ በ22 ዘርፎች እንደሚካሄድና የቱሪዝም ዘርፉን ማነቃቃት የሚያስችል መርኃ ግብር መሆኑን ነው ያስረዱት።
መርኃ ግብሩ ኢትዮጵያን በዘርፉ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ተወዳዳሪ እንደሚያደርጋት ጠቁመው፣ በውድድሩ 70 አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ለእይታ ይቀርባሉ ብለዋል።
የውድድሩ ዓላማ የተሻሉ ቴክኖሎጂዎችን በማበልጸግ ከገበያው ጋር ማስተሳሰር መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡
በ2016 በጀት ዓመት 81 ቴክኖሎጂዎች መልማታቸውንና በዘንድሮው በጀት ዓመት ደግሞ 180 ተሳታፊዎች 99 ቴክኖሎጂዎች በማልማት ሂደት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የአርበኝነት ምዕራፍ ጀምራለች ያሉት ሚኒስትሯ፤ የክህሎት ውድድሩ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025