የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የአፍሪካን ኢኮኖሚያዊ ውህደት ለማፋጠን የሴቶችን ተሳትፎ የበለጠ ማሳደግ ይገባል - አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ

May 8, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 29/2017(ኢዜአ)፦ የአፍሪካን ኢኮኖሚያዊ ውህደት ለማፋጠን የሴቶችን ተሳትፎ የበለጠ ማሳደግ እንደሚገባ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገለፁ።

6ኛው የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ(ኮሜሳ) ሴት ሥራ ፈጣሪዎች የንግድ ትርዒትና ኮንፍረንስ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በንግድ ትርዒቱ መክፈቻ ላይ እንዳሉት፣ አፍሪካ በ2063 ለማሳካት ከያዘቻቸው አጀንዳዎች አንዱ የሴቶችን እኩልነትና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መሆኑን አንስተዋል።

የተቀናጀና የተናበበ ስራ ለአፍሪካ ዘላቂ ዕድገት ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የኮሜሳ መስራች መሆኗን አንስተው፤ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ውጤታማ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ታደርጋለች ብለዋል።

ኢትዮጵያ ያደረገችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለግሉ ዘርፍ ምቹ ሁኔታ የፈጠረና ተወዳዳሪነትን ያሳደገ መሆኑንም ተናግረዋል።

የአፍሪካን ኢኮኖሚያዊ ውህደት ለማፋጠን የሴቶችን ተሳትፎ የበለጠ ማሳደግ እንደሚገባ ገልጸው፤ ኮሜሳ ለሴት ስራ ፈጣሪዎች እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።


የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) በበኩላቸው የኮሜሳ አባል ሀገራት ሴቶች በንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ ጉልህ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል።

የሚገጥማቸውን ፈተናዎች ተቋቁመው በንግድ ሥራ ውጤታማ የሆኑ ሴቶች በርካታ መሆናቸውንም ነው የጠቀሱት።

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የኢኮኖሚ ውህደት በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኑንና በዘርፉ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለይታ ለመፍትሄው እየሰራች እንደሆነም ተናግረዋል።

የበለፀገች አፍሪካን እውን ለማድረግ የኮሜሳ አባል ሀገራት የበለጠ ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባም ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር አምባሳደር ሳልማ ማሊካ፤ በአፍሪካውያን መካከል የሚደረገውን የንግድ ልውውጥ በማሳደግ የአህጉሪቱን የኢኮኖሚ ውህደት ማፋጠን ይገባል ብለዋል።

የአፍሪካ ህብረት የሴቶችን እኩልነት ለማረጋገጥና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ቀርፆ ተግባራዊ እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.