የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎች የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ምቹ ምህዳር ፈጥረዋል - ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ

May 13, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 4/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በወሰደቻቸው የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎች የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን በመሳብ እና የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግርን ለማሳካት በትክክለኛ መንገድ ላይ እንደምትገኝ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ገለጹ።

በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ 2025 የቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በፎረሙ መክፈቻ ባደረጉት ንግግር፥ ኢትዮጵያ በርካታ የለውጥ እርምጃዎች እየወሰደች መሆኑን ገልጸዋል።

የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎች እድገትን ለማስቀጠል፣ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እና መዋቅራዊ ሽግግርን ማሳካት እንደሚያስችሉ አስረድተዋል።


ይህም ኢትዮጵያ በትክክለኛው የዕድገት ጎዳና ላይ እንድትገኝ አድርጓታል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፥ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ብሩህ ነው ብለዋል።

ለውጭ ባለሀብቶች ዝግ ሆነው የቆዩ ዘርፎችን የመክፈት ሀገራዊ ሪፎርም፣ የህግና የፖሊሲ ማሻሻያዎችና በተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስትመንትን በመሳብ ረገድ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣታቸውን አንስተዋል።

የማበረታቻ ስርዓቶችም ባለሀብቶች ኢንቨስትመንታቸውን እንዲያስፋፉና ዘላቂነትን እንዲያረጋግጡ የሚያግዙ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ፎረሙ ኢትዮጵያ ያላትን የኢንቨስትመንት አቅም ለማሳየት ትልቅ ዕድል መሆኑን ጠቅሰው፥ የመድረኩ ተሳታፊዎችም የተሻሉ ልምዶችን እንዲለዋወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.