ደብረ ብርሃን፤ ግንቦት 6/2017(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት የቴሌኮም ዘርፉ ድጋፍ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ።
ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ በደብረ ብርሃን ከተማ ለሀይለማሪያም ማሞ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የኮምፒዩተርና ሌሎች ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ።
በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት፤ በኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታን ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት የቴሌኮም ዘርፉ እገዛና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።
በዚህ ረገድ ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ ለትምህርት ቤቱ ላደረገው እገዛ ምስጋናቸውን አቅርበው የትምህርት ዘርፉን መደገፍ ለዲጅታል ዘርፉ እድገት ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን ገልጸዋል።
የተደረገው ድጋፍ ዲጂታል ቴክኖሎጂን ለትምህርት ጥራትና ውጤታማነት በመጠቀም ወጣቶችን በእውቀትና ክህሎት አንጾ ለማሳደግ የሚያግዝ መሆኑንም ተናግረዋል።
በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሪጅናል የውጭ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሲሳይ ዘሪሁን፤ ኩባንያው ለትምህርት ቤቱ የ14 ዘመናዊ ደስክ ቶፕ ኮምፒዩተሮች ድጋፍ ማድረጉን አንስተው ዓላማውም የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ እውቀትን ለተማሪዎች ተደራሽ ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል።
በእለቱ ለትምህርት ቤቱ ከተደረገው ድጋፍ በተጨማሪ በአካባቢው በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ወገኖችም የእህልና ሌሎችም ምግብ ነክ ቁሳቁሶችን መለገሱ ታውቋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025