የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች የሀገርን ሁለንተናዊ እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚያግዙ ናቸው

May 15, 2025

IDOPRESS

አሶሳ፤ ግንቦት 6/2017(ኢዜአ):- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች የሀገርን ሁለንተናዊ እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚያግዙ መሆናቸውን በብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ/ር) ተናገሩ።

ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ በአሶሳ ከተማ እየተሰጠ ካለው የአመራሮች እና የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ስልጠና ጎን ለጎን በመደመር መጽሀፍ ገቢ እየተገነባ የሚገኘውን ሙዚየም፣ የአሶሳ ከተማ የኮሪደር ልማት እንዲሁም የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።


ከጉብኝቱ በኋላም በመደመር መጽሀፍ እየተገነባ የሚገኘው ሙዚየም የክልሉን ህዝቦች ባህል እና እሴት የሚያንፀባርቅ እና ለትውልድ እንዲተላለፉ የሚያደርግ ትልቅ ፕሮጀክት መሆኑን አንስተዋል።

ፕሮጀክቱ የመደመርን ፅንሰ ሃሳብ በተግባር የሚያሳይ ለጥናት እና ምርምር የሚያገለግል የብልጽግና እሳቤ ማሳያ መሆኑንም ገልጸዋል።

በመሆኑም በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች የሀገርን ሁለንተናዊ እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚያግዙ መሆናቸውን ተናግረዋል።


የግንባታ ሂደቱ 90 በመቶ የደርሰው ሙዚየሙ የቅርሶች ማስቀመጫ፣ ቤተመጻህፍት፣ ቴአትር ቤት እንዲሁም በክልሉ የሚገኙ ብሄር ብሄረሰቦች መገለጫዎችን የያዘ መሆኑን አንስተው እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማትም የከተማዋን ገጽታ የሚቀይር እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ነው ያሉት።

የኮሪደር ልማት በሁሉም አካባቢዎች በተጠናከረ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን አንስተው የከተሞች ዕድገት እና ዘመናዊነት ለኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ መሠረት የሚያኖር መሆኑንም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.