የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

መዲናዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፉ ስራዎች እየተከናወኑ ነው- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

May 19, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ግንቦት10 /2017 (ኢዜአ)፦መዲናዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፉ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ በአዲስ ዓለም ዓቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኤክስፖ (ETEX 2025) ጎብኝተዋል።

ከንቲባ አዳነች በዚሁ ወቅት፤ ከተማዋ ከሀገር አልፎ የዓለም አቀፍ እና አህጉረ አቀፍ ኮንፈረንስ የማዘጋጀት አቅም እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል።


ባለፉት አስር ቀናት ብቻ የኮንፈረንስ እና ኤክስፖዎች በመዲናዋ መከናወናቸውን ገልፀው፤ ይህም የከተማዋን ገቢ በማሳደግ በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።

በሀገሪቱ በቴክኖሎጂ ልማት ላይ ትልቅ ለውጥ እና እድገት እየተመዘገበ ይገኛልም ብለዋል።

ከተማዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

"ኢቴክስ 2025" ኤክስፖ ዲጂታል ኢትዮጵያን ለማረጋገጥ የተያዘውን ግብ ለማሳካት ጫፍ ላይ መድረሳችን አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።


የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በጋራ ያዘጋጁት በምስራቅ አፍሪካ ትልቁ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ 2025 በአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.