አዲስ አበባ፤ግንቦት 8/2017(ኢዜአ)፦በቡና ግብይት ስንሰለት እና በምርታማነት እድገት ላይ በተሰሩ ስራዎች ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ማሳደግ መቻሉን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) ገለፁ።
በበጀት አመቱ 10 ወራት ወደ ውጭ ከተላከ ቡና 1 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፥ መንግስት የቡና ምርትና ምርታማነትን በመጨመርና ጥራቱን በማሻሻል በአለም ገበያ ተፎካካሪነትን ማሳደግ ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው።
በዚህም በበጀት ዓመቱ አሥር ወራት 354 ሺህ ቶን ቡና በመላክ 1 ነጥብ 87 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን ገልጸዋል፡፡
ይህም በአገሪቱ የቡና የወጪ ንግድ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነ ከፍተኛ አፈጻጸም መመዝገቡን ነው ዳይሬክተሩ የተናገሩት።
አፈጻጸሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በመጠን 145 ሺህ ቶን ጭማሪ ማሳየቱን ገልጸው፤ በገቢ ረገድም 870 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ጭማሪ የተመዘገበበት መሆኑንም ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል።
ቡናን በስፋት መትከል፣ ያረጁ ቡናዎችን መጎንደልና ቡናን በብዛትና በጥራት ለማምረት አስችሏል ያሉት ዶክተር አዱኛ፤ በዚህም በሄክታር የሚገኘውን የቡና ምርት ማሳደግ መቻሉንና የግብይት ሰንሰለቱን በማሳጠር ላይ የተሰራው ስራ የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ማስቻሉንም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ለውጭ ገበያ የምታቀርበው የቡና ምርት ከአመት አመት በመጠንም በጥራትም እየጨመረ እንዲመጣ ማድረጉን ገልፀዋል።
በበጀት አመቱ ቀሪ ወራቶችም ከቡና ንግድ ለማግኘት የታቀደውን 2 ቢሊዮን ዶላር ከግብ ለማድረስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025