ወላይታ ሶዶ፤ግንቦት 8/2017 (ኢዜአ)፦የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢንቨስትመንት ቢሮ ቦታ ወስደው ለዓመታት ሳያለሙ በቆዩ 96 ፕሮጀክቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።
የክልሉ መንግስት የሥራ ኃላፊዎች በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።
የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ አጸደ አይዛ፥ በከተማዋ ለኢንቨስትመንት ተብለው የተወሰዱ ቦታዎችን ሳያለሙ ማስቀመጥ እንደማይቻልና አግባብ እንዳልሆነ ተናግረዋል።
የክልሉ መንግስት የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ፈጥነው ወደ ሥራ እንዲገቡ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል ብለዋል።
ይሁን እንጂ በክልሉ የወሰዱትን መሬት ሳያለሙ ለዓመታት አጥረው ባስቀመጡ 96 ፕሮጀክቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል።
ከእነዚህም መካከል 34 ፕሮጀክቶች ውላቸው እንዲቋረጥ የተደረገ ሲሆን ቀሪዎቹ ላይ የማስጠንቀቂያ እርምጃ የተወሰደ መሆኑን አስታውቀዋል።
የጉብኝቱ ዓላማ የሪጂዮ ፖሊ ከተሞችን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ለማሳደግ እና የባለሀብቶችን ጥያቄ ለመፍታት መሆኑን ገልፀው፥ ባለሀብቶች የሚያነሷቸውን ማነቆዎች በመፍታት ዘርፉን ለማነቃቃት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
በክልሉ በግብርናና በአገልግሎት እንዲሁም በኢንዱስትሪ ዘርፎች ከ1 ሺህ 700 በላይ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ስራ ላይ መሆናቸውንም ወይዘሮ አጸደ አመልክተዋል።
በክልሉ የኢንቨስትመንት ሥራዎችም ከ120 ሺህ በላይ ዜጉች የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸውም ጠቁመዋል።
የክልሉ መንግስት እያከናወነ ያለውን የቁጥጥርና ክትትል እንዲሁም የድጋፍ ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው፥ ባለሀብቶች የወሰዱትን መሬት በገቡት ውል መሰረት በማልማት የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025