ግንቦት፤ ግንቦት 11/2017(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ለመኸር እርሻ ጥቅም ላይ የሚውል የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ እንዲደርስ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮ ኃላፊው ጌቱ ገመቹ እንደገለጹት፣ ለመኸር እርሻ መደበኛ ኮምፖስትን ጨምሮ የተለያዩ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ተዘጋጅቶ ጥቅም ላይ ለማዋል እየተሰራ ነው።
የተፈጥሮ ማዳበሪያ የአፈር ለምነትን ለመጨመርና ምርታማነትን ለማሳደግ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቅሰው፣ በበጀት ዓመቱ 250 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ መደበኛ ኮምፖስት እና 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል ቫርሚ ኮምፖስት ተዘጋጅቶ ለአርሶ አደሩ እየተሰረጨ ነው።
በክልሉ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ማዘጋጃ ማዕከላት በመገንባት አርሶ አደሩ በዝግጅት ሂደቱ ግንዛቤውን የማሳደግ ሥራ መሰራቱንም ተናግረዋል።
በክልሉ የተፈጥሮ ማዳበሪያን ከማዘጋጀት ጎን ለጎን የአርሶ አደሩን የአፈር ማዳበሪያ ፍላጎትለሟሟላት በአሁኑ ወቅት ከ6 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ክልሉ ገብቶ ለአርሶ አደሩ እየተሰራጨ መሆኑንም ገለጸዋል።
በቡኖ በዴሌ ዞን በተፈጥሮ ማዳበሪያ ማዘጋጃ ማዕከል የአፈር ለምነት ባለሙያ መሃመድ ሱልጣን፤ ቫርሚ ኮምፖስት የአፈርን ለምነት በመጠበቅ፣ የአፈር አሲዳማነትን በመቀነስና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትልቅ ጠቀሜታ አለው ብለዋል።
ማዕከሉ ቫርሚ ኮምፖስት በማምረት ለአርሶ አደሩ ከማቅረብ ጎን ለጎን አርሶ አደሮችን በማሰልጠን የበኩሉን እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል።
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በሚገኝ የቫርሚ ኮምፖስት ማምረቻ ማዕከል ውስጥ የምትሰራው ብርሃኔ ሶቦቅሳ፤ ማዕከሉ ቫርሚ ኮምፖስት አምርቶ በተመጣጣኝ ዋጋ ለአርሶ አደሮች እያቀረበ ይገኛል።
በተጨማሪ አርሶ አደሩ በራሱ በማምረት እንዴት መጠቀም እንደሚችል በማዕከሉ በኩል ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ገልጻለች።
የተፈጥሮ ማዳበሪያው የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ከመጨመረ ባለፈ የአፈር ማዳበሪያ ለመግዛት የሚያወጣውን ወጪ ቀንሶለታልም ነው ያለችው።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025