ዲላ ፤ ግንቦት 12/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተሞችልማታዊ ሴፍቲኔቲ ፕሮግራም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖችን ኑሮ እያሻሻለ መሆኑን የክልሉ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ገለጸ።
የፌደራልና የክልሉ አመራር አባላት በጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ልማታዊ የሴፍቲኔት ፕሮግራም እንቅስቃሴን በመስክ ተመልክተዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ምክትል ሃላፊ ወይዘሮ የምስራች ገመዴ በወቅቱ እንዳሉት፤ ልማታዊ የሴፍቲኔቲ ፕሮግራም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖች ኑሮ ከማሻሻል ባለፈ የከተሞችን ገጽታ እየቀየረ ነው።
በተለይ በገቢ ማስገኛ ስራዎች፣ በከተማ ውበትና ፅዳት የመጡ ለውጦችን ይበልጥ በማጠናከር ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የሚደረገውን ሂደት ለማፋጠን እየተሰራ ነው ብለዋል።
በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የከተሞች የምግብ ዋስትናና ሴፍቲኔቲ ጽህፈት ቤት የዜጎች ተሳትፎና ሃብት ማፈላለግ ዴስክ ሃላፊ አቶ ሙሉዓለም ስሜ በበኩላቸው፤ ፕሮግራሙ በ87 ከተሞች ከ1 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ወገኖችን ተጠቃሚ በማድረግ ኑሯቸውን በዘላቂነት እንዲያሻሽሉ እያገዘ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህ ረገድ በዲላ ከተማ በአካባቢ ልማት የተሰማሩ ወገኖች ለራሳቸው ሃብት ከመፍጠራቸው ባለፈ የህብረተሰቡን ችግር እየፈቱ መሆናቸውን አንስተዋል።
ይህም የአካባቢ ልማት ስራን ቀጣይነት በማረጋገጥ ከተረጂነት መላቀቅ እንደሚቻል ማሳያ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መስፍን ዴምሴ(ዶ/ር)፤ በከተማው የቀጥታ ድጋፋ ጨምሮ 2 ሺህ 141 የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች የፕሮግራሙ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ይህም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖችን ኑሮ በማሻሻል የስራና የቁጠባ ባህል ያሳደገ መሆኑን አንስተው፤ በዘርፉ የመጡ ለውጦችን ለማጠናከር የመስክ ምልከታው ድርሻ የጎላ ስለመሆኑም ነው ያመለከቱት።
ከተጠቃሚዎች መካከል ወይዘሮ ፀሐይ ክፍሌ በሰጡት አስተያየት፤ በልማታዊ ሴፍቲነት ባገኙት የገንዝብ ድጋፍና የክህሎት ስልጠና ታግዘው በንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት እራሳቸውን በመቻል ነግድው ያተረፉት ከ180 ሺህ ብር በላይ ተቀማጭ ገንዝብ እንዳላቸው ጠቅሰዋል።
በመስክ ምልከታው ከፌደራል፣ ከአለም ባንክ፣ ከክልልና ከተማ አስተዳደሩ የተወጣጡ አመራር አባላትና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025